ሕዝቅኤል 18:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቶች ጎምዛዛ የወይን ፍሬ በሉ፥ የልጆችም ጥርሶች አጠረሰ፥ ብላችሁ ስለ እስራኤል ምድር የምትመስሉት ምሳሌ ምንድነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለ እስራኤል ምድር፣ “ ‘አባቶች ጐምዛዛ የወይን ፍሬ በሉ፤ የልጆችንም ጥርስ አጠረሰ’ እያላችሁ የምትመስሉት ተምሳሌት ምን ለማለት ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእስራኤል ምድር ተደጋግሞ የሚነገር ይህ ምሳሌ ምንድን ነው? ‘ወላጆች ጐምዛዛ የወይን ፍሬ በሉ፤ ነገር ግን የልጆቻቸውን ጥርስ አጠረሰ’ ይላሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በእስራኤል ልጆች፦ ‘አባቶች ጨርቋ የወይን ፍሬ በሉ፥ የልጆችም ጥርሶች ጠረሱ’ ብላችሁ በመካከላችሁ የምትመስሉት ምሳሌ ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ እስራኤል ምድር፦ አባቶች ጨርቋ የወይን ፍሬ በሉ፥ የልጆችም ጥርሶች ጠረሱ ብላችሁ የምትመስሉት ምሳሌ ምንድር ነው? |
አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም፤ እኔ ጌታ አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥
ለዓመፀኛ ቤት እንዲህ በል፦ እነዚህ ነገሮች ምን እንደ ሆኑ አታውቁምን? በላቸው። ንገራቸው፦ እነሆ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ ንጉሥዋንና ልዑሎችዋን ወሰደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ባቢሎን አመጣቸው።
እናንተ ግን፦ የአባትን ኃጢአት ልጁ ለምን አይሸከምም? ትላላችሁ። ልጅ ፍትሕንና ጽድቅን ቢያደርግ፥ ትእዛዜንም ሁሉ ቢጠብቅና ቢያደርገው በእርግጥ በሕይወት ይኖራል።
ለአሞንም ልጆች እንዲህ በላቸው፦ የጌታ እግዚአብሔርን ቃል ስሙ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ፥ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ፥ የይሁዳም ቤት ተማርከው በተወሰዱ ጊዜ እሰይ ብለሻልና፤
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች መላው የእስራኤል ቤት ናቸው፤ እነሆ፦ “አጥንቶቻችን ደርቀዋል ተስፋችንም ጠፍቶአል፤ ፈጽመን ተቆርጠናል” ይላሉ።
እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በኤፍሬም እጅና በተባባሪዎቹ በእስራኤል ነገዶች ያለውን የዮሴፍን በትር እወስዳለሁ፥ ከይሁዳ በትር ጋር አስቀምጣቸዋለሁ፥ አንድ በትር አደርጋቸዋለሁ፥ በእጄም አንድ ይሆናሉ።
ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት፥ አባቶቻችሁም በኖሩባት ምድር ይኖራሉ፤ እነርሱ፥ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ለዘለዓለም በእርሷ ይኖራሉ፤ አገልጋዬ ዳዊት ለዘለዓለም ልዑላቸው ይሆናል።
ነገር ግን፥ ሰው ሆይ! ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? የተሠራ ነገር የሠራውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ይለዋልን?