Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 12:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ምድር፦ “ቀኖቹ ረዝመዋል፥ ራእይም ሁሉ ጠፍቶአል” የምትሉት ይህ ምሳሌ ምንድነው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “የሰው ልጅ ሆይ፤ በእስራኤል ምድር፣ ‘ዘመኑ ረዝሟል፤ ራእዩ ሁሉ ከንቱ ሆኗል’ የምትሉት ይህ አባባል ምንድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “የሰው ልጅ ሆይ! ራእዩ ሁሉ ተግባራዊ ሳይሆን ቀኖቹ ተራዘሙ ተብሎ ስለ እስራኤል ምድር የሚነገረው ይህ ምሳሌ ምንድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 “የሰው ልጅ ሆይ! በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር፦ ዘመኑ ረዝ​ሞ​አል፤ ራእ​ዩም ሁሉ ጠፍ​ቶ​አል የም​ት​ሉት ምሳ​ሌው ምን​ድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ምድር፦ ዘመኑ ረዝሞአል ራእዩም ሁሉ ጠፍቶአል የምትሉት ምሳሌ ምንድር ነው?

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 12:22
12 Referencias Cruzadas  

እነርሱም፦ ቤቶች የሚሰሩበት ጊዜ ቅርብ አይደለምን? ይህች ከተማ ድስት ናት፥ እኛም ሥጋ ነን ብለዋል።


የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ የእስራኤል ቤት እንዲህ ይላሉ፦ የሚያየው ራእይ ለብዙ ዘመን ነው፥ እርሱም ለሩቅ ወራት ትንቢት ይናገራል።


ክፉውን ቀን ከእናንተ ታርቃላችሁን? የግፍንስ ወንበር ታቀርባላችሁን?


በዐይናችን እንድናይ እግዚአብሔር ይቸኩል፤ ሥራውንም ያፋጥን፤ የእስራኤልን ቅዱስ፤ የእርሱን ዕቅድ እንድናውቃት ትቅረብ፤ ትምጣም ለሚሉ ወዮላቸው!”


እነሆ በምሳሌ የሚናገር ሁሉ፦ “ሴት ልጇ እንደ እናቷ ናት” እያለ ምሳሌ ይመስልብሻል።


በጥፋት ላይ ጥፋት ይመጣል፥ ወሬም ወሬን ይከተላል፥ ከነቢይ ራእይን ይፈልጋሉ፥ ከካህን ሕግ፥ ከሽማግሌዎችም ምክር ይጠፋል።


የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


አሕዛብን እዩ፥ ተመልከቱም፤ እጅግ ተደነቁ፥ ተገረሙም፤ ቢነገራችሁ የማታምኑትን ሥራ በዘመናችሁ እሠራለሁና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios