ዳዊትም በምድረ በዳ ውስጥ ባለችው በአምባይቱ ሳለ ከጋድ ወገን የሆኑ እነዚህ በጋሻና በጦር ስልታቸው የተካኑ፥ ጽኑዓን ኃያላን፥ ተዋጊዎች፥ ወደ እርሱ መጡ፤ ፊታቸውም እንደ አንበሳ ፊት ነበረ፥ በተራራም ላይ እንደሚዘልል ሚዳቋ ፈጣኖች ነበሩ።
ሕዝቅኤል 1:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፊታቸውም ምስል የሰው ፊት፥ አራቱም በቀኝ በኩል የአንበሳ ፊት፥ በግራ በኩል የላም ፊት ነበራቸው፥ አራቱም ደግሞ የንስር ፊት ነበራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፊታቸውም እንዲህ ነበር፤ አራቱም እያንዳንዳቸው የሰው ፊት ነበራቸው፤ በቀኝ በኩል የአንበሳ ፊት፣ በግራ በኩልም የበሬ ፊት ነበራቸው፤ እያንዳንዳቸውም ደግሞ የንስር ፊት ነበራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያንዳንዱ ፍጥረት አራት የተለያዩ ፊቶች ነበሩት፤ ይኸውም ከፊት ለፊት የሰው መልክ የሚመስል፥ በስተቀኝ በኩል የአንበሳ መልክ፥ በስተግራ የበሬ ፊት፥ በስተ ኋላም የንስር መልክ የሚመስል ነበሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፊታቸው አምሳያ እንደዚህ ነው፦ ለአራቱ ሁሉ በቀኛቸው የሰው ፊትና የአንበሳ ፊት አላቸው፤ ለአራቱም ሁሉ በግራቸው የእንስሳ ፊትና የንስር ፊት አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፊታቸው አምሳያ እንደ ሰው ፊት ነበረ፥ ለአራቱም በስተ ቀኛቸው እንደ አንበሳ ፊት፥ በስተ ግራቸውም እንደ ላም ፊት ነበራቸው፥ ለአራቱም ደግሞ የንስር ፊት ነበራቸው። |
ዳዊትም በምድረ በዳ ውስጥ ባለችው በአምባይቱ ሳለ ከጋድ ወገን የሆኑ እነዚህ በጋሻና በጦር ስልታቸው የተካኑ፥ ጽኑዓን ኃያላን፥ ተዋጊዎች፥ ወደ እርሱ መጡ፤ ፊታቸውም እንደ አንበሳ ፊት ነበረ፥ በተራራም ላይ እንደሚዘልል ሚዳቋ ፈጣኖች ነበሩ።
እያንዳንዱም አራት አራት ፊት ነበሩት፥ አንደኛው ፊት የኪሩብ ፊት፥ ሁለተኛው ፊት የሰው ፊት፥ ሦስተኛው ፊት የአንበሳ ፊት፥ አራተኛውም ፊት የንስር ፊት ነበረ።
የሰው ፊት በአንድ ወገን ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ይመለከት ነበር፥ የአንበሳ ፊት ደግሞ በሌላው ወገን ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ይመለከት ነበር፤ በቤቱ ሁሉ ዙሪያ እንደዚህ ተቀርጾ ነበር።
በምሥራቅ በኩል ወደ ፀሐይ መውጫ የሚሰፍሩት እንደ ሠራዊቶቻቸው የይሁዳን ሰፈር ዓላማ የያዙት ይሆናሉ፤ የይሁዳ ልጆችም አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ።
ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፤ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፤ ሦስተኛውም እንስሳ የሰውን ፊት የሚመስል ፊት ነበረው፤ አራተኛውም እንስሳ የሚበር ንስር ይመስል ነበር።
ከሽማግሌዎቹም አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፥ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል፤” አለኝ።
በሰባተኛው ቀን ፀሓይ ከመጥለቋ በፊት የከተማው ሰዎች፥ “ከማር የጣፈጠ ምን ተገኝቶ? ከአንበሳስ ወዲያ ብርቱ ከየት መጥቶ” አሉት። ሳምሶንም መልሶ፥ “በጊደሬ ባላረሳችሁ፥ እንቈቅልሼንም ባልፈታችሁ” አላቸው።