ሕዝቅኤል 1:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ፊታቸው እንዲህ ነበረ። ክንፎቻቸውም ወደ ላይ ተዘርግተው ነበር፥ የእያንዳንዳቸውም ሁለት ክንፋቸው የተያያዙ ነበሩ፥ በሁለቱም ገላቸውን ይከድኑ ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 እንግዲህ ፊታቸው ይህን ይመስል ነበር፤ ክንፋቸውም ወደ ላይ ተዘርግቶ ነበር፤ እያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ክንፍ ነበራቸው፤ የእያንዳንዱም ክንፍ የሌላውን ክንፍ ይነካ ነበር፤ ሁለቱ ክንፎቻቸው ሰውነታቸውን ይሸፍኑ ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 የእያንዳንዱ እንስሳ ሁለት ክንፎች ወደ ላይ ከፍ ብለው ከእነርሱ ቀጥሎ ያለውን ፍጥረት የክንፎች ጫፍ ይነኩ ነበር፤ የቀሩት ሁለቱ ክንፎቻቸው ግን ተጣጥፈው አካላቸውን ይሸፍኑ ነበር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ክንፋቸውም በላይ ተዘርግቶ ነበር፤ የእያንዳንዱም ሁለት ሁለት ክንፋቸው የተያያዙ ነበሩ፤ ሁለት ሁለቱም ገላቸውን ይከድኑ ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ክንፋቸውም በላይ ተዘርግቶ ነበር፥ የእያንዳንዱም ሁለት ሁለት ክንፋቸው የተያያዙ ነበሩ፥ ሁለት ሁለቱም ገላቸውን ይከድኑ ነበር። Ver Capítulo |