Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 1:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የፊ​ታ​ቸው አም​ሳያ እን​ደ​ዚህ ነው፦ ለአ​ራቱ ሁሉ በቀ​ኛ​ቸው የሰው ፊትና የአ​ን​በሳ ፊት አላ​ቸው፤ ለአ​ራ​ቱም ሁሉ በግ​ራ​ቸው የእ​ን​ስሳ ፊትና የን​ስር ፊት አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ፊታቸውም እንዲህ ነበር፤ አራቱም እያንዳንዳቸው የሰው ፊት ነበራቸው፤ በቀኝ በኩል የአንበሳ ፊት፣ በግራ በኩልም የበሬ ፊት ነበራቸው፤ እያንዳንዳቸውም ደግሞ የንስር ፊት ነበራቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የፊታቸውም ምስል የሰው ፊት፥ አራቱም በቀኝ በኩል የአንበሳ ፊት፥ በግራ በኩል የላም ፊት ነበራቸው፥ አራቱም ደግሞ የንስር ፊት ነበራቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እያንዳንዱ ፍጥረት አራት የተለያዩ ፊቶች ነበሩት፤ ይኸውም ከፊት ለፊት የሰው መልክ የሚመስል፥ በስተቀኝ በኩል የአንበሳ መልክ፥ በስተግራ የበሬ ፊት፥ በስተ ኋላም የንስር መልክ የሚመስል ነበሩት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የፊታቸው አምሳያ እንደ ሰው ፊት ነበረ፥ ለአራቱም በስተ ቀኛቸው እንደ አንበሳ ፊት፥ በስተ ግራቸውም እንደ ላም ፊት ነበራቸው፥ ለአራቱም ደግሞ የንስር ፊት ነበራቸው።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 1:10
20 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም በም​ድረ በዳ ውስጥ ባለ​ችው በአ​ን​ባ​ዪቱ ሳለ ከጋድ ወገን የሆኑ እነ​ዚህ ጋሻና ጦር የሚ​ይዙ፥ ጽኑ​ዓን፥ ኀያ​ላን ሰል​ፈ​ኞች፥ ወደ እርሱ ተጠጉ፤ ፊታ​ቸ​ውም እንደ አን​በሳ ፊት ነበረ፤ በተ​ራ​ራም ላይ እን​ደ​ሚ​ዘ​ልል ሚዳቋ ፈጣ​ኖች ነበሩ።


በአ​ፍህ ትእ​ዛዝ ንስር ከፍ ከፍ ይላ​ልን? ጆፌ አሞ​ራስ ልጆ​ቹን አቅፎ ያድ​ራ​ልን?


በሬዎች በሌሉበት ስፍራ በረቱ ንጹሕ ነው፤ ብዙ እህል ግን በበሬዎች ኀይል ይገኛል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉና የሚ​ታ​ገሡ ግን ኀይ​ላ​ቸ​ውን ያድ​ሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወ​ጣሉ፤ ይሮ​ጣሉ፤ አይ​ታ​ክ​ቱ​ምም፤ ይሄ​ዳሉ፤ አይ​ራ​ቡ​ምም።


ይህን ዐስ​ቡና አል​ቅሱ፤ የተ​ሳ​ሳ​ታ​ችሁ ሆይ፥ ንስሓ ግቡ፤ ልባ​ች​ሁ​ንም መልሱ።


ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም አራት አራት ፊት፥ ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም አራት አራት ክንፍ ነበ​ሩት።


ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም አራት አራት ፊት ነበ​ሩት፤ አን​ደ​ኛው ፊት የኪ​ሩብ ፊት፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም የሰው ፊት፥ ሦስ​ተ​ኛው የአ​ን​በሳ ፊት፥ አራ​ተ​ኛ​ውም የን​ስር ፊት ነበረ።


በአ​ንድ ወገን ወደ አለው የዘ​ን​ባባ ዛፍ የሰው ፊት ይመ​ለ​ከት ነበር፤ በሌ​ላ​ውም ወገን ወደ አለው ዘን​ባባ የአ​ን​በሳ ፊት ይመ​ለ​ከት ነበር፤ በቤቱ ሁሉ ዙሪያ እን​ደ​ዚህ ተቀ​ርጾ ነበር።


“በአ​ዜብ በኩል በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው የሮ​ቤል ሰፈር ዓላማ ይሆ​ናል፤ የሮ​ቤ​ልም ልጆች አለቃ የሴ​ድ​ዮር ልጅ ኤሊ​ሱር ነበረ።


“በባ​ሕር በኩል እንደ ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው የኤ​ፍ​ሬም ሰፈር ዓላማ ይሆ​ናል፤ የኤ​ፍ​ሬም ልጆች አለቃ የኤ​ሜ​ሁድ ልጅ ኤሌ​ሳማ ነበረ።


“በመ​ስዕ በኩል እንደ ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው የዳን ሰፈር ዓላማ ይሆ​ናል፤ የዳ​ንም ልጆች አለቃ የአ​ሚ​ሳዲ ልጅ አክ​ያ​ዜር ነበረ።


በመ​ጀ​መ​ሪያ በም​ሥ​ራቅ በኩል የሚ​ሰ​ፍ​ሩት ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር የይ​ሁዳ ሰፈር ሰዎች ይሆ​ናሉ፤ የይ​ሁዳ ልጆ​ችም አለቃ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን ነበረ።


እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ እን​ዲሁ ንስሓ ስለ​ሚ​ገባ ስለ አንድ ኀጢ​ኣ​ተኛ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ፊት በሰ​ማ​ያት ደስታ ይሆ​ናል።”


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በአ​እ​ምሮ እንደ ሕፃ​ናት አት​ሁኑ፤ ነገር ግን ለክፉ ነገር እንደ ሕፃ​ናት ሁኑ፤ በዕ​ው​ቀ​ትም ፍጹ​ማን ሁኑ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ንስር እን​ደ​ሚ​በ​ርር ከሩቅ ሀገር፥ ከም​ድር ዳር ቋን​ቋ​ቸ​ውን የማ​ት​ሰ​ማ​ውን ሕዝብ፥


ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፤ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፤ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፤ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።


ከሽማግሌዎቹም አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፥ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል፤” አለኝ።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ቀን ፀሐይ ሳት​ገባ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ሰዎች፥ “ከማር የሚ​ጣ​ፍጥ ምን​ድን ነው? ከአ​ን​በ​ሳስ የሚ​በ​ረታ ማን ነው?” አሉት። ሶም​ሶ​ንም፥ “በጥ​ጃዬ ባላ​ረ​ሳ​ችሁ ኑሮ የእ​ን​ቆ​ቅ​ል​ሼን ትር​ጓሜ ባላ​ወ​ቃ​ች​ሁም ነበር” አላ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos