የእንበረም ልጆች አሮንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮንም ከሁሉ በላይ የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፥ እርሱና ልጆቹ፥ ለዘለዓለም በጌታ ፊት እንዲያጥኑና እንዲያገለግሉ፥ በስሙም ለዘለዓለም እንዲባርኩ ተለይተው ነበር።
ዘፀአት 30:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንም መልካም መዓዛ ያለው እጣን ማለዳ ማለዳ ይጠንበት፤ መብራቶቹን ሲያዘጋጅ ይጠነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሮን መብራቶቹን በሚያዘጋጅበት ጊዜ፣ በየማለዳው ደስ የሚያሰኝ ሽታ ዕጣን በመሠዊያው ላይ ያጢስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮን በየማለዳው መብራቶችን ለማዘጋጀት በሚመጣበት ጊዜ መልካም መዓዛ ያለውን ዕጣን በመሠዊያው ላይ ይጠን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንም በጎ መዓዛ ያለው የደቀቀ ዕጣን በውስጡ በየማለዳው ይጠንበት፤ መብራቶቹን ሲያዘጋጅ ይጠነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንም የጣፋጭ ሽቱ እጣን ይጠንበት፤ በማለዳ በማለዳ መብራቶቹን ሲያዘጋጅ ይጠነው። |
የእንበረም ልጆች አሮንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮንም ከሁሉ በላይ የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፥ እርሱና ልጆቹ፥ ለዘለዓለም በጌታ ፊት እንዲያጥኑና እንዲያገለግሉ፥ በስሙም ለዘለዓለም እንዲባርኩ ተለይተው ነበር።
ሰሎሞንም እንዲህ ሲል ወደ ጢሮስ ንጉሥ ወደ ኪራም ላከ፦ “ከአባቴ ከዳዊት ጋር እንዳደረግህ፥ የሚቀመጥበትንም ቤት ለመሥራት የዝግባ እንጨት እንደ ላክኽለት፥ እንዲሁ ለእኔ አድርግ።
እነሆ፥ ለእስራኤል ለዘለዓለም እንደ ታዘዘው በጌታ ፊት መዓዛው ያማረውን ሽቶ ዕጣን ለማጠን፥ የተቀደሰውንም ኅብስት ለማኖር፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በጥዋትና በማታ በሰንበታቱም በመባቻዎቹም በአምላካችንም በጌታ በዓላት ለማቅረብ ለአምላኬ ለጌታ ስም ቤት ልሠራለትና ልቀድስለት አሰብሁ።
ንጉሡንም ዖዝያንን እየተቃወሙ እንዲህ አሉት፦ “ዖዝያን ሆይ! ዕጣን ማጠን የተቀደሱት የአሮን ልጆች የካህናቱ ሹመት ነው እንጂ ለጌታ እንድታጥን ለአንተ አይገባህም፤ በድለሃልና ከመቅደሱ ውጣ፤ ከአምላክህም ከጌታ ዘንድ ክብር አያስገኝልህም።”
ደግሞም ዋና የመግቢያ ደጆችን ዘጉ፥ መብራቶቹንም አጥፍተዋል፥ በመቅደሱም ውስጥ ለእስራኤል አምላክ አላጠኑም፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አላቀረቡም።
ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “መልካም መዓዛ ያለው ቅመም፥ የሚንጠባጠብ ሙጫ፥ በዛጎል ውስጥ የሚገኝ ሽቱ፥ የሚሸት ሙጫና ንጹሕ እጣን ለራስህ ውሰድ፥ ሁሉም እኩል መጠን ይኑራቸው፤
ወይም በሐሰት የማለበትን ምንም ዓይነት ነገር ይመልስ፤ እርሱም የበደሉን መሥዋዕት በሚያቀርብበት ቀን በሙሉ የወሰደውን ነገር ይመልስ፥ በእርሱም ላይ አምስት እጅ ጨምሮበት ለባለቤቱ ይስጠው።
በቆሬና በእርሱም ተከታዮች ላይ የደረሰው እንዳይደርስበት፥ ከአሮን ልጆች ያልሆነ ሌላ ሰው በጌታ ፊት ዕጣንን ለማጠን እንዳይቀርብ፥ ጌታ በሙሴ እንደ ተናገረው፥ ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ አደረጋቸው።
ከእስራኤልም ነገድ ሁሉ ካህን ይሆነኝ ዘንድ፥ በመሠዊያዬ ላይ ይሠዋ ዘንድ፥ ዕጣንንም ያጥን ዘንድ ኤፋድንም በፊቴ እንዲለብስ ለእኔ መረጥሁት፤ የእስራኤልንም ልጆች የሚያቀርቡትን የሚቃጠል መሥዋዕት ለአባትህ ቤት ሰጠሁ።