Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 30:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 አሮን በየማለዳው መብራቶችን ለማዘጋጀት በሚመጣበት ጊዜ መልካም መዓዛ ያለውን ዕጣን በመሠዊያው ላይ ይጠን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “አሮን መብራቶቹን በሚያዘጋጅበት ጊዜ፣ በየማለዳው ደስ የሚያሰኝ ሽታ ዕጣን በመሠዊያው ላይ ያጢስ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አሮንም መልካም መዓዛ ያለው እጣን ማለዳ ማለዳ ይጠንበት፤ መብራቶቹን ሲያዘጋጅ ይጠነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አሮ​ንም በጎ መዓዛ ያለው የደ​ቀቀ ዕጣን በው​ስጡ በየ​ማ​ለ​ዳው ይጠ​ን​በት፤ መብ​ራ​ቶ​ቹን ሲያ​ዘ​ጋጅ ይጠ​ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አሮንም የጣፋጭ ሽቱ እጣን ይጠንበት፤ በማለዳ በማለዳ መብራቶቹን ሲያዘጋጅ ይጠነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 30:7
20 Referencias Cruzadas  

የቀዓት የበኲር ልጅ ዓምራም፥ የአሮንና የሙሴ አባት ነበር፤ አሮንና ዘሮቹ ለዘለቄታው ለንዋያተ ቅድሳት ኀላፊዎች እንዲሆኑ፥ እግዚአብሔርን በማምለክ ሥነ ሥርዓት ላይ ዕጣን እንዲያጥኑ፥ እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉና በስሙም ሕዝቡን እንዲባርኩ ተለይተው ነበር፤


ሕልቃና፥ ይሮሐም፥ ኤሊኤል፥ ቶሐ፥


ከዚህም በኋላ ለጢሮስ ንጉሥ ኪራም የሚከተለውን መልእክት ላከ፤ “አባቴ ንጉሥ ዳዊት ቤተ መንግሥቱን በሠራበት ጊዜ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ትልክለት እንደ ነበር ለእኔም ላክልኝ፤


አሁን እኔ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስን ለመሥራት በመዘጋጀት ላይ ነኝ፤ ይህም ቤተ መቅደስ እኔና ሕዝቤ በእግዚአብሔር ፊት ጣፋጭ ሽታ ያለውን ዕጣን የምናጥንበት የተቀደሰውን ኅብስት ሳናቋርጥ ለእግዚአብሔር የምናቀርብበት፥ በየቀኑ ጠዋትና ማታ፥ እንዲሁም በሰንበቶች፥ በወር መባቻዎችና በሌሎችም በተቀደሱ በዓላት እግዚአብሔር አምላካችንን ለማክበር የሚቃጠለውን መሥዋዕት የምናቀርብበት የተቀደሰ ስፍራ ይሆናል፤ የእስራኤል ሕዝብ ይህን ለዘለዓለም እንዲያደርጉ እግዚአብሔር አዞአል።


እንዲህም አሉት፦ “ዖዝያ ሆይ! አንተ ለእግዚአብሔር ዕጣን ታጥን ዘንድ አይገባህም፤ ይህን ለማድረግ የተመደቡት ለእግዚአብሔር የተለዩት የአሮን ልጆች የሆኑት ካህናት ብቻ ናቸው፤ ስለዚህ ከዚህ ከተቀደሰው ስፍራ ውጣ፥ እግዚአብሔር አምላክን አሳዝነሃል፤ ይህም ከእግዚአብሔር ዘንድ ክብርን የሚያስገኝልህ ድርጊት አይደለም።”


የቤተ መቅደሱን በር ሁሉ ዘጉ፤ መብራቶቹንም አጠፉ፤ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ዕጣንን ማጠን ወይም የሚቃጠል መሥዋዕትን ማቅረብ ተዉ፤


ጸሎቴን እንደ ዕጣን፥ የተዘረጉትን እጆቼን እንደ ማታ መሥዋዕት አድርገህ ተቀበል።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የእያንዳንዳቸው ሚዛን እኩል የሆነ ጣፋጭ ቅመሞችን ይኸውም የሚንጠባጠብ ፈሳሽነት ያለው ሙጫ፥ በዛጎል ውስጥ የሚገኝ ሽቱ፥ የሚሸት ሙጫና ጣፋጭ ሽታ ያለው ዕጣን ወስደህ፥


ይህንንም መሠዊያ ከቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ከተሰቀለው መጋረጃ ውጪ አኑረው፤ እኔም በዚያ ለአንተ እገለጥልሃለሁ፤


በየምሽቱም መብራቶቹን ሲያበራ እንዲሁ ያድርግ፤ ይህ የዕጣን መባ አቀራረብ በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ባለማቋረጥ የሚቀጥል መሆን አለበት።


እግዚአብሔርም ባዘዘው መሠረት ጣፋጭ ሽታ ያለውን ዕጣን በላዩ ላይ አጠነ።


ወይም በሐሰት ምሎ የወሰደውን ሁሉ አንድ አምስተኛ ጨምሮ ለባለቤቱ ይክፈል።


ይህም ሁኔታ የአሮን ዘር ያልሆነ ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር ዕጣን ያጥን ዘንድ ወደ መሠዊያው መቅረብ እንደማይገባው ለእስራኤላውያን ሁሉ ማስጠንቀቂያ ይሆናል፤ ይህ ካልሆነ ግን እንዲህ የሚያደርግ ሰው ሁሉ እንደ ቆሬና እንደ ተከታዮቹ ይጠፋል፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ነበር።


እንደ ካህናት አሠራር ልማድ ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ዕጣን ለማጠን ዕጣ ደረሰው።


እኛ ግን በመጸለይና የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር እንተጋለን።”


ሥርዓትህን ለያዕቆብ፥ ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራሉ፤ በፊትህ ዕጣን ያጥናሉ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም በመሠዊያህ ላይ ያቀርባሉ።


እርሱንም ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ወደ መሠዊያዬ እንዲወጣ፥ እጣን እንዲያጥን፥ በፊቴ ኤፉድ እንዲለብስ፥ የእኔ ካህን ይሆን ዘንድ መረጥሁት፤ ለቀድሞ አባትህ ልጆችም የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡትን የሚቃጠል መሥዋዕት ሰጠኋቸው።


ገና የቤተ መቅደሱ መብራት ሳይጠፋ ሳሙኤል የተቀደሰው የቃል ኪዳን ታቦት ባለበት መቅደስ ውስጥ ተኝቶ ነበር፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos