Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 30:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “መልካም መዓዛ ያለው ቅመም፥ የሚንጠባጠብ ሙጫ፥ በዛጎል ውስጥ የሚገኝ ሽቱ፥ የሚሸት ሙጫና ንጹሕ እጣን ለራስህ ውሰድ፥ ሁሉም እኩል መጠን ይኑራቸው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን አለው፤ “ተመጣጣኝ በማድረግ የጣፋጭ ሽቱ ቅመሞች፣ የሚንጠባጠብ ሙጫ፣ በዛጐል ውስጥ የሚገኝ ሽቱ፣ የሚሸት ሙጫ እና ንጹሕ ዕጣን ወስደህ፣

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የእያንዳንዳቸው ሚዛን እኩል የሆነ ጣፋጭ ቅመሞችን ይኸውም የሚንጠባጠብ ፈሳሽነት ያለው ሙጫ፥ በዛጎል ውስጥ የሚገኝ ሽቱ፥ የሚሸት ሙጫና ጣፋጭ ሽታ ያለው ዕጣን ወስደህ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ጣፋጭ ሽቱ ውሰድ፤ የሚ​ን​ጠ​ባ​ጠብ ሙጫ፥ በዛ​ጎል ውስጥ የሚ​ገኝ ሽቱ፥ የሚ​ሸ​ት​ትም ሙጫ፥ ጥሩም ዕጣን ውሰድ፤ የሁ​ሉም መጠን ትክ​ክል ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ጣፋጭ ሽቱ ውሰድ፤ የሚንጠባጠብ ሙጫ፥ በዛጎል ውስጥ የሚገኝ ሽቱ፥ የሚሸትትም ሙጫ፥ ጥሩም እጣን ውሰድ፤ የሁሉም መጠን ግን ትክክል ይሁን።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 30:34
20 Referencias Cruzadas  

ትልቅ ለሌዋውያን፥ ለመዘምራን፥ ለበረኞቹ እንደ ሕጉ የተሰጣቸውን የእህሉን ቁርባንና ዕጣኑን፥ ዕቃዎቹንም፥ የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም አሥራት፥ ለካህናቱም የሆነውን የማንሣት ቁርባን አስቀድሞ ያስቀመጡበትን ታላቁን ጓዳ አዘጋጅቶለት ነበር።


ለመብራት የሚሆን ዘይት፥ ለቅባት የሚሆን ዘይትና ለጣፋጭ ዕጣን የሚሆን ቅመም፥


“ምርጥ የሆኑትን ቅመሞች ለራስህ ውሰድ፤ ፈሳሽ ከርቤ አምስት መቶ ሰቅል፥ ግማሽ ይኸውም ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል የቀረፋ ቅመም፥ የጠጅ ሣርም እንዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥


እንደ እርሱ ዓይነት የሚቀምም ሰው ወይም ከእርሱ በሌላው ላይ የሚያፈስስ ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።’”


ቀማሚ እንደሚቀምመው፥ በጨው የተቀመመ፥ ንጹሕና ቅዱስ አድርገህ ዕጣን አዘጋጅ።


አሮንም መልካም መዓዛ ያለው እጣን ማለዳ ማለዳ ይጠንበት፤ መብራቶቹን ሲያዘጋጅ ይጠነው።


የቅባቱን ዘይት፥ ለመቅደሱ የሚሆን መልካም መዓዛ ያለውን ዕጣን እንዳዘዝሁህ ሁሉ እንዲሁ ያድርጉ።”


የዕጣኑን መሠዊያና መሎጊያዎቹን፥ የቅባቱን ዘይት፥ ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን፥ የድንኳኑን ደጃፍ መጋረጃ፤


የተቀደሰ የቅባት ዘይት፥ ንጹሕና መልካም መዓዛ ያለውን ዕጣን ቀማሚ እንደሚሠራው አደረገ።


መዓዛም እንደ ከርቤና እንደ ዕጣን የሆነችው፥ ከልዩ ከነጋዴ ቅመም ሁሉ የሆነችው፥ ይህች ከምድረበዳ እንደ ጢስ ምስሶ የወጣችው ማን ናት?


ለሚቃጠል መሥዋዕት በጎችህን አላቀረብህልኝም፤ በሌላም መሥዋዕትህ አላከበርኸኝም፤ በእህልም ቁርባን አላስቸገርሁህም፤ በዕጣንም አላደከምሁህም።


በጌታም ፊት ካለው መሠዊያ ላይ ያለውን የእሳት ፍም በጥናው ሞልቶ ያመጣል፥ ከተወቀጠውም ከመዐዛው ያማረ ዕጣን በሁለቱ የእጁ መዳፎች ሙሉ ዘግኖ ይወስዳል፤ ወደ መጋረጃውም ውስጥ ያመጣዋል።


“ማናቸውም ሰው የእህል ቁርባን ለጌታ ሲያቀርብ ቁርባኑ ከመልካም ዱቄት ይሁን፤ ዘይትም ያፈስበታል፥ ዕጣንም ይጨምርበታል፤


ዘይትም ታፈስበታለህ፥ ዕጣንም ትጨምርበታለህ፤ የእህል ቁርባን ነው።


ለጌታም በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ተደርጎ፥ ለእንጀራው የመታሰቢያ ቁርባን እንዲሆን በሁለቱ ተርታ ላይ ንጹሕ የሆነ ዕጣን አድርግ።


“እርሱም ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ለማቅረብ በቂ ገንዘብ ባይኖረው፥ ስለ ሠራው ኃጢአት እንደ ቁርባኑ አድርጎ የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ ክፍል መልካም ዱቄት ለኃጢአት መሥዋዕት ያመጣል፤ የኃጢአት መሥዋዕት ነውና ዘይት አያፈስበትም፥ ዕጣንም አይጨምርበትም።


“የካህኑም የአሮን ልጅ አልዓዛር በመብራቱ ዘይት መዓዛውም በሚያምር ዕጣን ላይ፥ ሁልጊዜም በሚቀርበው በእህሉ ቁርባንና በቅባቱ ዘይት ላይ ይሾም፤ ማደሪያውን ሁሉ፥ በእርሱም ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ መቅደሱንና ዕቃውን ይቆጣጠር።”


ዕጣንም የተሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወርቅ ሙዳይ፤


ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅ፥ ዕጣንና ከርቤ አቀረቡለት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos