ዘፀአት 30:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ምርጥ የሆኑትን ቅመሞች ለራስህ ውሰድ፤ ፈሳሽ ከርቤ አምስት መቶ ሰቅል፥ ግማሽ ይኸውም ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል የቀረፋ ቅመም፥ የጠጅ ሣርም እንዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ምርጥ ቅመሞችን፣ ዐምስት መቶ ሰቅል ፈሳሽ ከርቤ፣ ግማሽ ይኸውም ሁለት መቶ ዐምሳ ሰቅል ጣፋጭ ቀረፋ፣ ሁለት መቶ ዐምሳ ሰቅል ከሙን፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ምርጥ የሆኑ ቅመሞችን፥ ስድስት ኪሎ ግራም ፈሳሽ ከርቤ፥ ሦስት ኪሎ ግራም ጣፋጭ ሽታ ያለውን ቀረፋ፥ ሦስት ኪሎ ግራም ጣፋጭ ሽታ ያለውን የጠጅ ሣርና፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንተም ክቡሩን ሽቱ ውሰድ፤ የተመረጠ የከርቤ አበባ አምስት መቶ ሰቅል፥ የዚህም ግማሽ ጣፋጭ ቀረፋ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፤ ያማረ የጠጅ ሣርም እንዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም ክቡሩን ሽቱ ውሰድ፤ የተመረጠ ከርቤ አምስት መቶ ሰቅል፥ ግማሽም ጣፋጭ ቀረፋ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥ የጠጅ ሣርም እንዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥ |
ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣንን፥ ከሩቅም አገር የከበረውንም ዘይት ታመጡልኛላችሁ? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን አልቀበለውም፥ ሌላ መሥዋዕታችሁም ደስ አያሰኘኝም።
የሳባና የራዕማ ነጋዴዎች እነዚህ ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ምርጥ በሆኑ ቅመማ ቅመሞች ሁሉ፥ በክበረ ድንጋይ ሁሉና በወርቅ ሸቀጥሽን ይለውጡ ነበር።
“የካህኑም የአሮን ልጅ አልዓዛር በመብራቱ ዘይት መዓዛውም በሚያምር ዕጣን ላይ፥ ሁልጊዜም በሚቀርበው በእህሉ ቁርባንና በቅባቱ ዘይት ላይ ይሾም፤ ማደሪያውን ሁሉ፥ በእርሱም ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ መቅደሱንና ዕቃውን ይቆጣጠር።”
ከዚያም ሳሙኤል የዘይቱን ብርሌ ወስዶ፥ ዘይቱን በሳኦል ራስ ላይ ካፈሰሰ በኋላ ሳመው፥ እንዲህም አለው፤ “በርስቱ ላይ ገዥ ትሆን ዘንድ ጌታ ቀብቶህ የለምን?