እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፦ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ።
ዘፀአት 24:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የጌታን ቃሎች ሁሉ ጻፈ፤ በማለዳ ተነሥቶ ከተራራው በታች መሠዊያንና ዐሥራ ሁለት ሐውልቶች ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሙሴ እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ ጻፈ። በማግስቱም ማልዶ ተነሥቶ፣ በተራራው ግርጌ መሠዊያን ሠራ፤ ዐሥራ ሁለቱን የእስራኤልን ነገዶች የሚወክሉ ዐሥራ ሁለት የድንጋይ ዐምዶችን አቆመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ ጻፈ፤ በማግስቱም ጠዋት በማለዳ በተራራው ሥር መሠዊያ ሠራ፤ ለእያንዳንዱም የእስራኤል ነገድ አንድ የድንጋይ ዐምድ አኖረ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ጻፈ፤ ማለዳም ተነሣ፤ ከተራራውም በታች መሠዊያን ሠራ፤ ዐሥራ ሁለትም ድንጋዮችን ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ አቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ጻፈ ማለዳም ተነሣ፥ ከተራራውም በታች መሠዊያን፥ አሥራ ሁለትም ሐውልቶች ለአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ሠራ። |
እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፦ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ።
ለዚህ የእግዚአብሔር ቤት ምረቃ አንድ መቶ ወይፈኖች፥ ሁለት መቶ አውራ በጎች፥ አራት መቶ የበግ ጠቦቶችን፥ ስለ ኃጢአትም መሥዋዕት እንደ እስራኤል ነገዶች ቍጥር ለእስራኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየሎች አቀረቡ።
ጌታም ሙሴን፦ “ይህንን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፥ በኢያሱም ጆሮ አኑረው፥ የአማሌቅን መታሰቢያ ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና” አለው።
“ለእስራኤል ልጆች ተናገር፥ ከእነርሱም ከእያንዳንዱ ከየአባቶቻቸው ቤት አንድ አንድ በትር፥ ከአለቆቻቸው ሁሉ ከየአባቶቻቸው ቤት ዐሥራ ሁለት በትሮች፥ ውሰድ፤ የእያንዳንዱንም ስም በየበትሩ ላይ ጻፍ።
በመንግሥቴም ከእኔ ማዕድ ትበላላአችሁ፥ እንዲሁም ትጠጣላችሁ፤ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ላይም ለመፍረድ በዙፋኖች ላይ ትቀመጣላችሁ።
የተሰጠኝን ጸጋ አውቀው፥ ምሰሶዎች መስለው የሚታዩ ያዕቆብ፥ ኬፋና ዮሐንስ፥ እነርሱ ወደ ተገረዙት እኛ ወደ አሕዛብ እንድንሄድ ለእኔና ለበርናባስ የኅብረት ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤
ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “በአምላካችሁ በጌታ ታቦት ፊት በዮርዳኖስ መካከል እለፉ፤ ከእናንተም ሰው ሁሉ በእስራኤል ልጆች ነገድ ቍጥር በትከሻው ላይ አንድ አንድ ድንጋይ ከዚያ ይሸከም።