መክብብ 8:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለክፉ መልካም አይሆንም፤ በእግዚአብሔርም ፊት አይፈራምና ዘመኑ እንደ ጥላ አትረዝምም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ክፉዎች አምላክን ስለማይፈሩ መልካም አይሆንላቸውም፤ ዕድሜያቸው እንደ ጥላ አይረዝምም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰዎች ግን ምንም ነገር አይሰምርላቸውም፤ እግዚአብሔርንም ስለማይፈሩ ሕይወታቸው እንደ ጥላ ያልፋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለኃጥእ ግን ደኅንነት የለውም፥ በእግዚአብሔርም ፊት አይፈራምና ዘመኑ እንደ ጥላ አትረዝምም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለኀጥእ ግን ደኅንነት የለውም፥ በእግዚአብሔርም ፊት አይፈራምና ዘመኑ እንደ ጥላ አትረዝምም። |
እግዚአብሔር የሚያደርገው ሁሉ ለዘለዓለም እንደሚኖር አወቅሁ፥ ምንም የሚጨመርበት ወይም የሚቀነስለት የለም፥ እግዚአብሔርም ሰዎች ይፈሩ ዘንድ አደረገ።
ከፍ ካለው ባለ ሥልጣን በላይ ሌላ ከፍ ያለ ይመለከታልና፥ ከእነርሱም በላይ ደግሞ ሌሎች ከፍ ይላሉና በአገሩ ድሆች ሲገፉ፥ ፍርድና ጽድቅም ሲነጠቅ ባየህ ጊዜ በዚህ ነገር አትደነቅ።
ሰው በከንቱ የሕይወቱ ቀናት ቍጥር ና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማነው? ወይስ ከፀሐይ በታች ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ለሰው ማን ይነግረዋል?
መንፈስን ለማገድ በመንፈስ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፥ በሞቱም ቀን ላይ ሥልጣን የለውም፥ በጦርነትም ውስጥ መሰናበቻ የለም፥ ክፋትም ሠሪውን አያድነውም።
ከዚያም ወዲያ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚኖር ሕፃን፥ ወይም ዕድሜውን ያልፈጸመ ሽማግሌ አይገኝም፤ ጎልማሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞታልና፥ የመቶ ዓመት ሳይሆነው የሚሞት እንደተረገመ ኃጢአተኛ ይታያል።
ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ፍርዳቸውም ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል!