Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መክብብ 5:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ከፍ ካለው ባለ ሥልጣን በላይ ሌላ ከፍ ያለ ይመለከታልና፥ ከእነርሱም በላይ ደግሞ ሌሎች ከፍ ይላሉና በአገሩ ድሆች ሲገፉ፥ ፍርድና ጽድቅም ሲነጠቅ ባየህ ጊዜ በዚህ ነገር አትደነቅ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ብዙ ሕልምና ብዙ ቃል ከንቱ ነው፤ ስለዚህ አምላክን ፍራ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ብዙ ሕልምና ብዙ ልፍለፋ ከንቱ ነው፤ ከዚህስ ይልቅ እግዚአብሔርን ፍራ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ብዙ ሕልም፥ እን​ዲሁ ደግሞ ብዙ ቃል ከንቱ ነውና፤ አንተ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽ​መህ ፍራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ብዙ ሕልም ባለበት ዘንድ፥ እንዲሁም ደግሞ ብዙ ቃል ባለበት ስፍራ በዚያ ብዙ ከንቱ ነገር አለ፥ አንተ ግን እግዚአብሔርን ፍራ።

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 5:7
11 Referencias Cruzadas  

እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ከንቱ ቃል ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤


የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፥ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፥ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ።


ኃጢአተኛ መቶ ጊዜ ክፉን ቢሠራ ዘመኑም ረጅም ቢሆን፥ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት በፊቱም ለሚፈሩት መልካም እንደሚሆን አውቃለሁ፥


አላዋቂዎች ደስ አያሰኙትምና ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ ለመፈጸም አትዘግይ፥ የተሳልኸውን ፈጽመው።


እግዚአብሔር የሚያደርገው ሁሉ ለዘለዓለም እንደሚኖር አወቅሁ፥ ምንም የሚጨመርበት ወይም የሚቀነስለት የለም፥ እግዚአብሔርም ሰዎች ይፈሩ ዘንድ አደረገ።


ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና፥ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ ጌታን በመፍራት ኑር፥


እግዚአብሔርን የሚፈራ በሁሉም ይዋጣለታልና ይህን ብትይዝ፥ ከዚያም ደግሞ እጅህን ባታርቅ መልካም ነው።


ለክፉ መልካም አይሆንም፤ በእግዚአብሔርም ፊት አይፈራምና ዘመኑ እንደ ጥላ አትረዝምም።


ደግሞም ከፀሐይ በታች በፍርድ ስፍራ ክፋት፥ በጽድቅም ስፍራ ክፋት እንዳለ አየሁ።


ይህን ሁሉ አየሁ፥ ከፀሐይም በታች ወደ ለተደረገው ሥራ ሁሉ ልቤን ሰጠሁ፥ ሰው ሰውን ለመጉዳት ገዢ የሚሆንበት ጊዜ አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios