ዘዳግም 2:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ አምላካችንም እርሱን አሳልፎ ሰጠን፤ እርሱንና ልጆቹን፥ ሕዝቡንም ሁሉ መታን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችን እግዚአብሔር በእጃችን ላይ ጣለው፤ እኛም፣ እርሱን ከወንድ ልጆቹና ከመላው ሰራዊቱ ጋራ አንድ ላይ መታነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችን በእኛ እጅ ስለ ጣለው እርሱንና ልጆቹን፥ ያለውንም ሰው ሁሉ ገደልን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችንም እግዚአብሔር እርሱን አሳልፎ በእጃችን ሰጠን፤ እርሱንም፥ ልጆቹንም፥ ሕዝቡንም ሁሉ መታን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላካችንም እግዚአብሔር እርሱን አሳልፎ ሰጠን፤ እርሱንም ልጆቹንም ሕዝቡንም ሁሉ መታን። |
ድንበርህንም ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረበዳ እስከ ወንዙ ድረስ አደርጋለሁ፤ በምድሪቱ የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁና፥ ከፊትህ ታባርራቸዋለህ።
ቂጣ አልበላችሁም፤ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣችሁም፤ ይህን ያደረግሁት እኔ እግዚአብሔር ጌታ እንደሆንኩ እንድታውቁ ነው።
ጌታም ለአባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው፤ ከጠላቶቻቸውም ሁሉ ማንም ሰው ሊቋቋማቸው አልቻለም፤ ጌታም ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው።
ጌታም ጌዴዎንን፦ ከአንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝቶአል፥ ስለዚህ እስራኤል፦ እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ እኔ ምድያምን በእጃቸው አሳልፌ አልሰጣቸውም።