Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 136 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌታን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና።

2 የአማልክትን አምላክ አመስግኑ፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና።

3 የጌቶችን ጌታ አመስግኑ፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

4 ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

5 ሰማያትን በጥበቡ የሠራውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

6 ምድርን በውኃ ላይ ያጸናውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

7 ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

8 ፀሐይን በቀን ላይ እንድትሠለጥን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

9 ጨረቃንና ከዋክብትን በሌሊት እንዲሠለጥኑ ያደረገ፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

10 ከበኩራቸው ጋር ግብጽን የመታውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

11 እስራኤልንም ከመካከላቸው ያወጣውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

12 በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

13 የኤርትራን ባሕር በየክፍሉ የከፈለውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

14 እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

15 ፈርዖንንና ሠራዊቱን በኤርትራ ባሕር የጣለውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

16 ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

17 ታላላቅ ነገሥታትን የመታውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

18 ብርቱዎችንም ነገሥታት የገደለውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

19 የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

20 የባሳንን ንጉሥ ዐግን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

21 ምድራቸውን ርስት አድርጎ የሰጠውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

22 ለባርያው ለእስራኤል ርስት፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና።

23 እኛን በመዋረዳችን አስቦናልና፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

24 ከጠላቶቻችንም እጅ አድኖናልና፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

25 ለሥጋ ሁሉ ምግብን የሚሰጥ፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና።

26 የሰማይን አምላክ አመስግኑ፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos