እንዲህም፦ “ኑ ለእኛ ከተማ እንመስርት፥ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበታተንም ስማችንን እናስጠራ” አሉ።
ዘዳግም 1:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዴትስ እንወጣለን? ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ቁመቱም ከእኛ ይረዝማል፥ ከተሞቹም ታላላቆች የተመሸጉም እስከ ሰማይም የደረሱ ናቸው፥ የዔናቅንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው፥’ ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን አወኩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ ወዴት መሄድ እንችላለን? ወንድሞቻችን፣ ‘ሰዎቹ ከእኛ ይልቅ ብርቱዎችና ቁመተ ረዣዥሞች፣ ከተሞቹም ትልልቆችና እስከ ሰማይ በሚደርስ ቅጥር የታጠሩ ናቸው፤ እንዲያውም በዚያ የዔናቅን ልጆች አይተናቸዋል’ ሲሉ እንድንፈራ አድርገውናል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ እዚያ የምንሄደው ለምንድን ነው? እንፈራለን፤ የላክናቸውም ሰዎች በዚያ የሚኖሩት ሁሉ ብርቱዎችና በቁመታቸውም ከእኛ ይበልጥ ረጃጅሞች መሆናቸውን፥ እንዲሁም ርዝመታቸው እስከ ሰማይ የሚደርስ የግንብ ቅጽሮች ባሉአቸው ከተሞች የሚኖሩ መሆናቸውን ነገሩን፤ እጅግ ግዙፋን የሆኑ የዔናቅ ልጆችንም አይተዋል።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወዴት እንወጣለን? ሕዝቡ ታላቅና ብዙ ነው፤ ከእኛም ይጠነክራሉ፤ ከተሞቹም ታላላቆች፥ የተመሸጉም፥ እስከ ሰማይም የደረሱ ናቸው፤ የረዐይትንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን አስፈሩት።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወዴት እንወጣለን? ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ቁመቱም ከእኛ ይረዝማል፥ ከተሞቹም ታላላቆች የተመሸጉም እስከ ሰማይም የደረሱ ናቸው፥ የዔናቅንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን አስፈሩት። |
እንዲህም፦ “ኑ ለእኛ ከተማ እንመስርት፥ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበታተንም ስማችንን እናስጠራ” አሉ።
እነርሱም ለምን ታለቅሳለህ? ሲሉህ እንዲህ በላቸው፦ ወሬ ስለሚመጣ ነው፥ ልብ ሁሉ ይቀልጣል፥ እጆች ሁሉ ይዝላሉ፥ ነፍስ ሁሉ ትደክማለች፥ ጉልበት ሁሉ እንደ ውኃ ይፈስሳል፥ እነሆ ይመጣል ይፈጸማልም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ይህንንም ነገር ሰምተን ልባችን ቀለጠ፤ ጌታ አምላካችሁም በላይ በሰማይ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተነሣ ከእግዲህ ወዲያ ሰው ሁሉ ሐሞተ ቢስ ሆኖአል።
ኢያሱንም እንዲህ አሉት፦ “በእውነት ጌታ አገሩን ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶአል፤ ከእኛም የተነሣ በአገሩ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ በፍርሃት ቀልጠዋል።”
ሰዎቹንም እንዲህ አለቻቸው፦ “ጌታ ምድሪቱን እንደ ሰጣችሁ፥ ከእናንተም የተነሣ በፍርሃት መዋጣችንን፥ በምድሪቱም የሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ በፍርሃት እንደ ቀለጡ አወቅሁ።
የይሁዳ ሰዎች በኬብሮን በሚኖሩ ከነዓናውያን ላይ ዘመቱ፤ ኬብሮን ቀደም ሲል ቂርያት-አርባዕ ተብላ ትጠራ ነበር፤ እነርሱም ሼሻይን፥ አሒማንንና ታልማይኖችን ድል አደረጉ።