Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢያሱ 11:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በጋዛ በጌትም በአዛጦንም ጥቂቶች ቀሩ እንጂ በእስራኤል ልጆች ምድር ከዔናቅ ልጆች ማንም አልቀረም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከእነዚህም ጥቂቶቹ ብቻ በጋዛ፣ በጋትና በአሽዶድ ሲቀሩ፣ በእስራኤል የቀሩ የዔናቅ ዘሮች ግን አልነበሩም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከዐናቅ ዘሮች በእስራኤል ምድር የተረፈ አልነበረም፤ ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ በጋዛ፥ በጋትና በአሽዶድ ይኖሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በጋዛ፥ በጌ​ትም፥ በአ​ዛ​ጦ​ንም ከቀ​ሩት በቀር በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ከኤ​ና​ቃ​ው​ያን ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በጋዛ በጌትም በአዛጦንም ጥቂቶች ቀሩ እንጂ በእስራኤል ልጆች ምድር ከዔናቅ ልጆች ማንም አልቀረም።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 11:22
19 Referencias Cruzadas  

ከጋት ከተማ የመጣ፥ ቁመቱ ስድስት ክንድ ከስንዝር የነበር ጎልያድ ተብሎ የሚጠራ አንድ ግዙፍ ዋነኛ ጀግና ሰው፥ ከፍልስጥኤማውያን ሰፈር ወጣ።


ከአቃሮንም ጀምሮ እስከ ባሕሩ ድረስ በአዛጦን አጠገብ ያሉት ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር።


የአሦር ንጉሥ ሳርጎን ተርታንን በሰደደ ጊዜ እርሱም ወደ አዛጦን በመጣ ጊዜ አዛጦንም ወግቶ በያዛት ጊዜ፥


ወጥቶም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ፥ የጌትንና የየብናን የአዞጦንንም ቅጥር አፈረሰ፤ በአዛጦንና በፍልስጥኤማውያንም አገር ከተሞችን ሠራ።


ከዚህም በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን መታ፥ አስገበራቸውም፥ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ጌትንና መንደሮችዋን ወሰደ።


በሪዓና ሽማዕ የጌትን ሰዎች ያሳደዱ የኤሎን ሰዎች የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤


ከሦስት ዓመት በኋላ ግን ሁለቱ የሺምዒ አገልጋዮች የማዕካ ልጅ ወደ ሆነው አኪሽ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ጋት ንጉሥ ኰብልለው ሄዱ፤ ሺምዒም ባርያዎቹ በጋት መኖራቸው ተነገረው፤


ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ከማረኩ በኋላ፥ ከአቤንኤዘር ወደ አሽዶድ ወሰዱት።


እነዚህም አሕዛብ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዦች፥ ከነዓናውያን በሙሉ፥ ሲዶናውያንና ከበኣል አርሞንዔም ተራራ እስከ ሐማትስ መግቢያ ባሉት የሊባኖስ ተራሮች የሚኖሩ ኤዊያውያን ነበሩ።


ፊልጶስ ግን በአዛጦን ተገኘ፤ ወደ ቂሣርያም እስኪመጣ ድረስ እየዞረ በከተማዎች ሁሉ ወንጌልን ይሰብክ ነበር።


ስለ እነርሱም፥ ‘በዔናቅ ልጆች ፊት ማን መቆም ይችላል?’ ሲባል የሰማኸው፥ አንተም የምታውቃቸው፥ ግዙፍና ረጃጅም ሕዝቦች የዔናቅ ልጆች ናቸው።


ካሌብም ሦስቱን የዔናቅን ልጆች ሴሲንና አኪመንን ተላሚንም ከዚያ ስፍራ አሳደደ። እነዚህም የዓናቅ ትውልድ ነበሩ።


ደግሞም የይሁዳ ሰዎች ጋዛን ከነግዛቶቿ፥ አስቀሎን ከነግዛቶቿ፥ አቃሮን ከነግዛቶቿ ያዙ።


እስከ ጋዛም ድረስ በመንደሮች ተቀምጠው የነበሩትን ኤዋውያንን ከካፍቶር የወጡ ካፍቶራውያን አጠፉአቸው፥ በስፍራቸውም ሰፈሩ።


ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ ድረስ የጎሶምንም ምድር ሁሉ እስከ ገባዖን ድረስ መታ።


አዛጦንና የተመሸጉና ያልተመሸጉ መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ያልተመሸጉም መንደሮችዋ፥ እስከ ግብጽ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ዳርቻ ድረስ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios