እግዚአብሔርም ከአባቴ ቤት ባወጣኝ ጊዜ አልኋት፦ ‘በገባንበት አገር ሁሉ ለእኔ የምታደርጊው ወሮታ ይህ ነው፦ ወንድሜ ነው ብለሽ ስለ እኔ ተናገሪ።’”
ሐዋርያት ሥራ 5:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጴጥሮስም “የጌታን መንፈስ ትፈታተኑ ዘንድ ስለምን ተስማማችሁ? እነሆ፥ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር በደጅ ነው፤ አንቺንም ያወጡሻል፤” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጴጥሮስም፣ “የጌታን መንፈስ ትፈታተኑ ዘንድ እንዴት እንዲህ ተስማማችሁ? እነሆ፤ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች ተመልሰው እግራቸው ደጃፍ ላይ ነው! አንቺንም ይዘው ይወጣሉ” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “የእግዚአብሔርን መንፈስ ለመፈታተን እንዴት ተስማማችሁ? እነሆ! ባልሽን ቀብረው የሚመለሱት ሰዎች በበር ናቸው፤ አንቺንም ወስደው ይቀብሩሻል” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጴጥሮስም፥ “እንግዲህ የእግዚአብሔርን መንፈስ ትፈታተኑት ዘንድ እንዴት ተባበራችሁ? እነሆ፥ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግሮች በበር ናቸው፤ አንቺንም ይወስዱሻል” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጴጥሮስም፦ “የጌታን መንፈስ ትፈታተኑ ዘንድ ስለ ምን ተስማማችሁ? እነሆ፥ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር በደጅ ነው አንቺንም ያወጡሻል” አላት። |
እግዚአብሔርም ከአባቴ ቤት ባወጣኝ ጊዜ አልኋት፦ ‘በገባንበት አገር ሁሉ ለእኔ የምታደርጊው ወሮታ ይህ ነው፦ ወንድሜ ነው ብለሽ ስለ እኔ ተናገሪ።’”
ወዲያውኑም ኤልሳዕን ይዞ የሚመጣ መልእክተኛ ላከ። በዚህም ጊዜ ኤልሳዕ ሊጐበኙት ከመጡ ጥቂት ሽማግሌዎች ጋር በቤት ውስጥ ነበር፤ የንጉሡ መልእክተኛ ከመድረሱም በፊት ኤልሳዕ ሽማግሌዎቹን “ያ ነፍሰ ገዳይ እኔን ለማስገደል አንድ ሰው ልኮአል! እነሆ፥ እርሱ እዚህ በሚደርስበት ጊዜ በሩን ዝጉ፤ ወደ ውስጥም እንዲገባ አትፍቀዱለት፤ ንጉሡም እርሱን ተከትሎ መጥቶ በኋላው ይገኛል” አላቸው።
እርሱም የዚያን ስፍራ ስም ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው፥ ይህም ስለ እስራኤል ልጆች ጥልና “ጌታ በመካከላችን ነው ወይስ አይደለም?” በማለት ጌታን ስለተፈታተኑት ነው።
እጆቻቸው ክፉ ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ልዑሉና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጉናሉ።
በግብጽ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግሁትን ክብሬንና ተአምራቴን ያዩ እነዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ እኔን ስለ ተፈታተኑኝ፥ ድምፄንም ስላልሰሙ፥
ነገር ግን አፍ ሁሉ እንዲዘጋና ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ ሥር እንዲሆን፤ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንደሚናገር እናውቃለን፤