ሐዋርያት ሥራ 23:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነጋም ጊዜ አይሁድ ጳውሎስን እስኪገድሉት ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ በመሐላ ተስማሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በነጋም ጊዜ፣ አይሁድ ተሰብስበው በማሤር ጳውሎስን እስኪገድሉ ድረስ እህል ውሃ ላለመቅመስ ተማማሉ። በዚህ ሤራ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በነጋ ጊዜ አይሁድ ተሰበሰቡና “ጳውሎስን ሳንገድል እህል አንበላም፤ ውሃም አንጠጣም” ብለው ተማማሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋም ጊዜ አይሁድ ተሰብስበው፥ ጳውሎስን እስኪገድሉት ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ ተስማምተው ተማማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጠባም ጊዜ አይሁድ ጳውሎስን እስኪገድሉት ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ በመሐላ ተስማሙ። |
ስለዚህ እርሷ “በእነዚያ ነቢያት ላይ ያደረግኸውን እኔም ነገ ልክ በአሁኑ ሰዓት በአንተ ላይ ሳላደርግብህ ብቀር አማልክት በሞት ይቅሠፉኝ!” ስትል ወደ ኤልያስ የዛቻ መልእክት ላከች።
ንጉሡም ድምፁን ከፍ በማድረግ “የዛሬይቱ ጀንበር ከመጥለቅዋ በፊት የሳፋጥ ልጅ የኤልሳዕ ራስ ሳይቆረጥ ቢያድር እግዚአብሔር እኔን በሞት ይቅጣኝ!” ሲል ተናገረ።
የቀሩት ሕዝብ፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ በር ጠባቂዎቹ፥ መዘምራን፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ ከምድር ሕዝቦች ወደ እግዚአብሔር ሕግ ራሳቸውን የለዩ ሁሉ፥ ሚስቶቻቸው፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው፥ የሚያውቁትና የሚያስተውሉት ሁሉ፥
እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ በግ ጠቦት ሆንሁ፤ እነርሱም፦ “ዛፉን ከነፍሬው እናጥፋ፥ ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታወስ ከሕያዋን ምድር እናስወግደው” ብለው ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እናንተና ሚስቶቻችሁ በአፋችሁ፦ ‘ለሰማይ ንግሥት ለማጠን የመጠጥንም ቁርባን ለእርሷ ለማፍሰስ የተሳልነውን ስእለታችንን በእርግጥ እንፈጽማለን’ ብላችሁ ተናገራችሁ በእጃችሁም አደረጋችሁት፤ እንግዲህ ስእለታችሁን አጽኑ ስእለታችሁንም ፈጽሙ።
እንግዲህ አንተ በጅ አትበላቸው፤ እስኪገድሉት ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ ተማምለው ከእነርሱ ከአርባ የሚበዙ ሰዎች ያደቡበታልና፤ አሁንም የተዘጋጁ ናቸው፤ የአንተንም ምላሽ ይጠብቃሉ፤” አለው።
በዚህም ሰው አይሁድ ሤራ እንደሚያደርጉበት ባመለከቱኝ ጊዜ ወዲያውኑ ወደ አንተ ላኩት፤ ከሳሾቹንም ደግሞ በፊትህ እንዳይከሱት ዘንድ አዘዝኋቸው።
ብዙ ጊዜ በጉዞ ተንከራትቼአለሁ፤ በወንዝ አደጋ፥ በወንበዴዎች አደጋ፥ በወገኔ በኩል ከሚመጣ አደጋ፥ በአሕዛብ በኩል ያለ አደጋ፥ በከተማ አደጋ፥ በምድረ በዳ አደጋ፥ በባሕር አደጋ፥ በሐሰተኛ ወንድሞች በኩል አደጋ ነበረብኝ፤
ለአሕዛብ እንዳንናገር በመከልከል እነርሱ እንዳይድኑ ያደርጋሉ፤ በዚህም ያለማቋረጥ የኃጢአታቸውን መስፈርያ ይሞላሉ፤ ነገር ግን በመጨረሻ የእግዚአብሔር ቁጣው ይመጣባቸዋል።
በዚያን ጊዜም ኢያሱ እንዲህ ብሎ ማለ፦ “ይህችን ከተማ ኢያሪኮን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በጌታ ፊት ርጉም ይሁን፤ መሠረትዋን ሲጀምር በኩር ልጁ ይጥፋ፥ በርዋንም ሲያቆም ታናሹ ልጁ ይጥፋ።”
የእስራኤል ልጆች ግን እርም በሆነው ነገር በደሉ፤ ከይሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እርሱም የከርሚ ልጅ፥ የዘንበሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥ እርም ከሆነው ነገር ወሰደ፤ የጌታም ቁጣ በእስራኤል ልጆች ላይ ነደደ።
እርም የሆነውም ነገር የተገኘበት ሰው የጌታን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል ፈጽሟልና እርሱና የእርሱ የሆነው ነገር ሁሉ በእሳት ይቃጠል።’ ”
ሳኦል፥ “ዛሬ ጠላቶቼን ከመበቀሌ በፊት፥ እስከ ማታ ድረስ እህል የሚበላ ሰው የተረገመ ይሁን” ብሎ ሕዝቡን አስምሎ ስለ ነበር፥ በዚያች ዕለት የእስራኤል ሰዎች ተጨንቀው ዋሉ፤ ስለዚህ ከሕዝቡ አንድም እህል የቀመሰ አልነበረም።