ጌታም በሴሎናዊው በአሒያ አድርጎ ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረውን ቃል እንዲያጸና ከጌታ ዘንድ ተወስኖ ነበርና ንጉሡ ሕዝቡን አልሰማም።
2 ዜና መዋዕል 25:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እየተናረ ሳለ ንጉሡ እንዲህ አለው፦ “በውኑ አንተ የንጉሡ አማካሪ ልትሆን ሾመነሃልን? ተው፤ እንዲገድሉህ ለምን ትሻለህ?” ነቢዩም፦ “ይህን አድርገሃልና፥ ምክሬንም አልሰማህምና ጌታ ሊያጠፋህ እንዳሰበ አወቅሁ” ብሎ ተወ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በመናገር ላይ ሳለ፣ ንጉሡ፣ “ለመሆኑ አንተን የንጉሥ አማካሪ አድርገን ሾመንሃልን? ዝም አትልም እንዴ! መሞት ትፈልጋለህ?” አለው። ነቢዩም ዝም አለ፤ ሆኖም፣ “ይህን አድርገሃልና ምክሬንም አልሰማህምና፤ አምላክ ሊያጠፋህ እንደ ወሰነ ዐውቃለሁ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነቢዩ ገና ንግግሩን ሳይፈጽም አሜስያስ “ለመሆኑ አንተን የንጉሡ አማካሪ አድርገን የሾምንህ ከመቼ ወዲህ ነው? ይልቅስ ንግግርህን አቁም፤ አለበለዚያ እገድልሃለሁ!” አለው። ነቢዩም ለአንድ አፍታ ንግግሩን ቆም ካደረገ በኋላ “ይህን ሁሉ በማድረግህና የእኔን ምክር ለመስማት እምቢ በማለትህ እግዚአብሔር ሊያጠፋህ መወሰኑን አሁን ዐወቅሁ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ይህን ሲናገር ንጉሡ አሜስያስ፥ “በውኑ የንጉሡ አማካሪ ልትሆን ሹሜሃለሁን? ቅጣት እንዳያገኝህ ተጠንቀቅ” አለው። ነቢዩም፥ “ይህን አድርገሃልና፥ ምክሬንም አልሰማህምና እግዚአብሔር ሊያጠፋህ እንዳሰበ አወቅሁ” ብሎ ዝም አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ሲናገር ንጉሡ “በውኑ አንተ የንጉሡ አማካሪ ልትሆን ሾመነሃልን? ተው፤ ቅጣትን ስለ ምን ትሻለህ?” አለው። ነቢዩም “ይህን አድርገሃልና፥ ምክሬንም አልሰማህምና እግዚአብሔር ሊያጠፋህ እንዳሰበ አወቅሁ” ብሎ ተወ። |
ጌታም በሴሎናዊው በአሒያ አድርጎ ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረውን ቃል እንዲያጸና ከጌታ ዘንድ ተወስኖ ነበርና ንጉሡ ሕዝቡን አልሰማም።
አሳም በባለ ራእዩ ላይ ተቈጣ፤ ስለዚህም ነገር ተቈጥቶአልና በቊራኛ አስሮ በወህኒ ቤት አኖረው፤ በዚያን ጊዜም አሳ፥ ከሕዝቡ አያሌ ሰዎችን አሠቃየ።
የጌታም መንፈስ በካህኑ በዮዳሄ ልጅ በዘካርያስ ላይ መጣ፤ እርሱም በሕዝቡ ፊት ቆሞ እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘የጌታን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ? ለእናተም አሳካላችሁም፤ ጌታን ስለ ተዋችሁ እርሱ ትቶአችኋል።’ ”
ስለዚህም የጌታ ቁጣ በአሜስያስ ላይ ነደደ እንዲህ ብሎ የሚናገረውን ነቢይም ላከበት፦ “ሕዝባቸውን ከአንተ እጅ ያላዳኑትን የአሕዛብን አማልክት ለምን ፈለግሃቸው?”
የይሁዳም ንጉሥ አሜስያስ ተማክሮ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮአካዝ ልጅ ወደ ኢዮአስ እንዲህ ብሎ ላከ፦ “ና፥ እርስ በርሳችን ፊት ለፊት እንተያይ።”
ክፋትሽ ይቀጣሻል ክህደትሽ ይገሥጽሻል፤ ጌታን አምላክሽን መተውሽ ምን ያኽል ክፉና መራራ ነገር እንደሆነ እወቂም፥ ተመልከቺም፤ እኔን መፍራት በአንቺ ውስጥ የለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እኔ አልላክኋቸውምና፤ ነገር ግን እኔ እንዳሳድዳችሁ፥ እናንተና ትንቢት የሚነግሩአችሁ ነቢያትም እንድትጠፉ፥ በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገራሉ፥ ይላል ጌታ።”
‘በጌታ ቤት አለቃ ሆነህ እያበደ ትንቢት የሚናገርን ሰው ሁሉ በመንቈርና በዛንጅር አስረህ እንድታኖረው ጌታ በካህኑ በዮዳሄ ፋንታ ካህን አድርጎሃል።
ወደ መቅደስ ገብቶ በማስተማር ላይ ሳለ ሊቃነ ካህናትና የሕዝብ ሽማግሌዎች ወደ እርሱ መጥተው “እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?” አሉት።
“የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፥ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ፥ ጌታ አምላካችሁ መንፈሱን አደንድኖታልና ልቡንም አጽንቶታልና።”
ሰዎች እውነተኛውን ትምህርት የማይታገሱበት፤ ይልቁንም ጆሮዎቻቸውን የሚኮረኩራቸውን ነገር በመሻት ለራሳቸው ምኞት የሚመቹ አስተማሪዎችን የሚሰበስቡበት ጊዜ ይመጣልና።
እነዚህም ሁለት ነቢያት በምድር የሚኖሩትን ስላሠቃዩ በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ዕጣ ደስ ይላቸዋል፤ በደስታም ይኖራሉ፤ እርስ በርሳቸውም ስጦታ ይሰጣጣሉ።
ሰውስ በሰው ቢበድል እግዚአብሔር ይታደገዋል፤ ሰው ግን ጌታን ቢበድል ስለ እርሱ የሚለምን ማን ነው?” እነርሱ ግን ጌታ ሊገድላቸው ወድዷልና የአባታቸውን ቃል አልሰሙም።