2 ዜና መዋዕል 21:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእርሱም የኢዮሣፍጥ ልጆች ዓዛርያስ፥ ይሒኤል፥ ዘካርያስ፥ ዔዛርያስ፥ ሚካኤል፥ ሰፋጥያስ የሚባሉ ወንድሞች ነበሩት፤ እነዚህ ሁሉ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሣፍጥ ልጆች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢዮሆራም ወንድሞች የሆኑት የኢዮሣፍጥ ልጆችም ዓዛርያስ፣ ይሒኤል፣ ዘካርያስ፣ ዔዛርያስ፣ ሚካኤልና ሰፋጥያስ ይባላሉ። እነዚህ ሁሉ የእስራኤል ንጉሥ የኢዮሣፍጥ ልጆች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሣፍጥ ልጅ የሆነው ኢዮራም ስድስት ወንድሞች ነበሩት፤ እነርሱም ዐዛርያስ፥ ይሒኤል፥ ዘካርያስ፥ ዐዛርያ፥ ሚካኤልና ሸፋጥያ ተብለው የሚጠሩ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእርሱም የኢዮሣፍጥ ልጆች አዛርያስ፥ ኢይሔል፥ ዘካርያስ፥ ዔዛርያስ፥ ሚካኤል፥ ሰፋጥያስ የሚባሉ ስድስት ወንድሞች ነበሩት፤ እነዚህ ሁሉ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሣፍጥ ልጆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእርሱም የኢዮሣፍጥ ልጆች ዓዛርያስ፥ ይሒኤል፥ ዘካርያስ፥ ዔዛርያስ፥ ሚካኤል፥ ሰፋጥያስ የሚባሉ ወንድሞች ነበሩት፤ እነዚህ ሁሉ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሣፍጥ ልጆች ነበሩ። |
ካህናትንና ሌዋውያንንም ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፦ “ወደ ይሁዳ ከተሞች ውጡ፥ የአምላካችሁንም ቤት በየዓመቱ ለማደስ ከእስራኤል ሁሉ ገንዘብን ሰብስቡ፤ ነገሩንም ፈጥናችሁ አድርጉ።” ሌዋውያን ግን ቸል አሉ።
ድል ለነሡትም ለደማስቆ አማልክት፦ “የሶሪያን ነገሥታት አማልክት ረድተዋቸዋልና እኔን እንዲረዱኝ እሠዋላቸዋለሁ” ብሎ ሠዋላቸው። ነገር ግን ለእርሱና ለእስራኤል ሁሉ እንቅፋት ሆኑ።
አካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በከተማይቱም በኢየሩሳሌም ቀበሩት፤ ነገር ግን ወደ እስራኤል ነገሥታት መቃብር አላገቡትም፤ ልጁም ሕዝቅያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
የምናሴም የቀረው ነገር፥ ወደ አምላኩም የጸለየው ጸሎት፥ በእስራኤልም አምላክ በጌታ ስም የነገሩት የነቢያት ቃላት፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል።
ከነቢዩ ከሳሙኤል ዘመን ጀምሮ እንደዚህ ያለ ፋሲካ በእስራኤል ዘንድ ከቶ ተከብሮ አያውቅም፤ ከእስራኤልም ነገሥታት ሁሉ ኢዮስያስና ካህናቱ፥ ሌዋውያኑም፥ በዚያም የተገኙ የይሁዳና የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩት እንዳከበሩት ያለ ፋሲካ ያከበረ የለም።