Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 33:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የምናሴም የቀረው ነገር፥ ወደ አምላኩም የጸለየው ጸሎት፥ በእስራኤልም አምላክ በጌታ ስም የነገሩት የነቢያት ቃላት፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በምናሴ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ተግባር፣ ወደ አምላኩ ያቀረበው ጸሎቱና ባለራእዮች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም የነገሩት ቃል በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፏል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ምናሴ ያደረገው ሌላ ነገር ሁሉ፥ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ያቀረበው ጸሎት፥ ነቢያት በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ለምናሴ የተናገሩአቸው ቃላት ጭምር፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግበው ይገኛሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በት​እ​ዛ​ዝህ ለሚ​ሆ​ነው ይቅ​ርታ ስፍር ቍጥር የለ​ውም፤ ገናና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ብቻ ነህና፥ ይቅር ባይ፥ ከቍጣ የራ​ቅህ፥ ይቅ​ር​ታህ የበዛ፥ የሰ​ው​ንም ኀጢ​አት የም​ታ​ስ​ተ​ሰ​ርይ አንተ ነህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የምናሴም የቀረው ነገር፥ ወደ አምላኩም የጸለየው ጸሎት፥ በእስራኤልም አምላክ በእግዚአብሔር ስም የነገሩት የነቢያት ቃል፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 33:18
15 Referencias Cruzadas  

ሰሎሞን ያደረገው ሌላው ነገር፥ ያከናወነው ተግባርና ጥበቡ ሁሉ በሰሎሞን የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቧል።


ንጉሥ ኢዮርብዓም ያደረጋቸው ሌሎች ነገሮች ሁሉ፥ የተዋጋቸው ጦርነቶችና አገዛዙም እንዴት እንደ ነበር ሁሉም ነገር በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።


ናዳብ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።


እግዚአብሔርም እስራኤልንና ይሁዳን የሚያስጠነቅቁ መልእክተኞችንና ነቢያትን በመላክ “ከክፉ መንገዳችሁ ሁሉ ተመለሱ፤ አገልጋዮቼ በሆኑት ነቢያትና ባለ ራእዮች አማካይነት ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለእናንተም በሰጠሁት ሕጎችና ትእዛዞች የተጻፈውን ሥርዓቴን ጠብቁ” ብሎ ነግሮአቸው ነበር።


የቀረውም የፊተኛውና የኋለኛው የኢዮሣፍጥ ነገር፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ውስጥ በሚገኘው በአናኒ ልጅ በኢዩ ታሪክ ተጽፎአል።


ለእርሱም የኢዮሣፍጥ ልጆች ዓዛርያስ፥ ይሒኤል፥ ዘካርያስ፥ ዔዛርያስ፥ ሚካኤል፥ ሰፋጥያስ የሚባሉ ወንድሞች ነበሩት፤ እነዚህ ሁሉ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሣፍጥ ልጆች ነበሩ።


የሕዝቅያስም የቀረው ነገር፥ ቸርነቱም፥ እነሆ፥ በአሞጽ ልጅ በነቢዩ በኢሳይያስ ራእይ በይሁዳና በእስራኤልም ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል።


ጌታም ምናሴንና ሕዝቡን ተናገራቸው፤ ግን አልሰሙትም።


ደግሞም ጸሎቱ፥ ጌታም እንደ ተለመነው፥ ኃጢአቱና መተላለፉ ሁሉ፥ ራሱንም ሳያዋርድ የኮረብታው መስገጃዎችን የሠራበት የማምለኪያ ዐፀዱንና የተቀረጹትንም ምስሎች የተከለበት ስፍራ፥ እነሆ፥ በባለ ራእዮቹ ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።


ጌታ የሚደብት የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል፤ ዐይኖቻችሁን፥ ነቢያትንም ጨፍኖባችኋል፤ ራሶቻችሁን ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል።


ባለ ራእዮችን፦ “አትመልከቱ” ይላሉ፥ ነቢያትንም፦ “ጣፋጩንና አታላዩን ነገር እንጂ ቅኑን ነገር አትንገሩን፤


አሜስያስም አሞጽን እንዲህ አለው፦ “ባለ ራእዩ ሆይ! ሂድ ወደ ይሁዳም ምድር ሽሽ፥ በዚያም እንጀራን ብላ፥ በዚያም ትንቢትን ተናገር፤


ትንቢተኞች ይዋረዳሉ፥ ጠንቋዮችም ያፍራሉ፤ ሁሉም ከንፈራቸውን ይሸፍናሉ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ መልስ የለምና።


ቀደም ሲል በእስራኤል ዘንድ አንድ ሰው እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሲሄድ፥ “ኑ፥ ወደ ባለ ራእዩ እንሂድ” ይል ነበር፤ ዛሬ ነቢይ የሚባለው በዚያ ጊዜ ባለ ራእይ ይባል ነበርና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos