Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 21:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ለእ​ር​ሱም የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጆች አዛ​ር​ያስ፥ ኢይ​ሔል፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ዔዛ​ር​ያስ፥ ሚካ​ኤል፥ ሰፋ​ጥ​ያስ የሚ​ባሉ ስድ​ስት ወን​ድ​ሞች ነበ​ሩት፤ እነ​ዚህ ሁሉ የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጆች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የኢዮሆራም ወንድሞች የሆኑት የኢዮሣፍጥ ልጆችም ዓዛርያስ፣ ይሒኤል፣ ዘካርያስ፣ ዔዛርያስ፣ ሚካኤልና ሰፋጥያስ ይባላሉ። እነዚህ ሁሉ የእስራኤል ንጉሥ የኢዮሣፍጥ ልጆች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ለእርሱም የኢዮሣፍጥ ልጆች ዓዛርያስ፥ ይሒኤል፥ ዘካርያስ፥ ዔዛርያስ፥ ሚካኤል፥ ሰፋጥያስ የሚባሉ ወንድሞች ነበሩት፤ እነዚህ ሁሉ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሣፍጥ ልጆች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሣፍጥ ልጅ የሆነው ኢዮራም ስድስት ወንድሞች ነበሩት፤ እነርሱም ዐዛርያስ፥ ይሒኤል፥ ዘካርያስ፥ ዐዛርያ፥ ሚካኤልና ሸፋጥያ ተብለው የሚጠሩ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ለእርሱም የኢዮሣፍጥ ልጆች ዓዛርያስ፥ ይሒኤል፥ ዘካርያስ፥ ዔዛርያስ፥ ሚካኤል፥ ሰፋጥያስ የሚባሉ ወንድሞች ነበሩት፤ እነዚህ ሁሉ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሣፍጥ ልጆች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 21:2
10 Referencias Cruzadas  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መሳ​ፍ​ን​ትና ንጉሡ አፈሩ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነው” አሉ።


ኢዮ​ራ​ምም በአ​ባቱ መን​ግ​ሥት ላይ ተነ​ሥቶ በጸና ጊዜ ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ፥ ሌሎ​ች​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን መሳ​ፍ​ንት በሰ​ይፍ ገደለ።


ይሁ​ዳ​ንም ዞሩ፤ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ሁሉ ሌዋ​ው​ያ​ን​ንና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ሰብ​ስ​በው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጡ።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ከቤ​ቱም ጋር መል​ካም ሠር​ቶ​አ​ልና በዳ​ዊት ከተማ ከነ​ገ​ሥ​ታቱ ጋር ቀበ​ሩት።


ካህ​ና​ት​ንና ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም ሰብ​ስቦ፥ “ወደ ይሁዳ ከተ​ሞች ውጡ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም ቤት በየ​ዓ​መቱ ለማ​ደስ የሚ​በቃ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ገን​ዘ​ብን ሰብ​ስቡ፤ ነገ​ሩ​ንም ፈጥ​ና​ችሁ አድ​ርጉ” አላ​ቸው። ሌዋ​ው​ያን ግን አላ​ፋ​ጠ​ኑም።


በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በአ​ካዝ ምክ​ን​ያት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁ​ዳን አዋ​ረ​ደው፤ እርሱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ ርቆ​አ​ልና።


ንጉ​ሡም፥ “የመ​ቱ​ኝን የደ​ማ​ስ​ቆን አማ​ል​ክት እፈ​ል​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የሶ​ር​ያን ንጉሥ እር​ሱን ረድ​ተ​ው​ታ​ልና እኔ​ንም ይረ​ዱኝ ዘንድ እሠ​ዋ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለ። ነገር ግን ለእ​ር​ሱና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዕን​ቅ​ፋት ሆኑ።


አካ​ዝም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ነገር ግን ወደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አላ​ገ​ቡ​ትም፤ ልጁም ሕዝ​ቅ​ያስ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


በት​እ​ዛ​ዝህ ለሚ​ሆ​ነው ይቅ​ርታ ስፍር ቍጥር የለ​ውም፤ ገናና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ብቻ ነህና፥ ይቅር ባይ፥ ከቍጣ የራ​ቅህ፥ ይቅ​ር​ታህ የበዛ፥ የሰ​ው​ንም ኀጢ​አት የም​ታ​ስ​ተ​ሰ​ርይ አንተ ነህ።


ከነ​ቢ​ዩም ከሳ​ሙ​ኤል ዘመን ጀምሮ እን​ደ​ዚህ ያለ ፋሲካ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ከቶ አል​ተ​ደ​ረ​ገም፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ኢዮ​ስ​ያ​ስና ካህ​ናቱ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ በዚ​ያም የተ​ገኙ የይ​ሁ​ዳና የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖ​ሩት እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት ያለ ፋሲካ ያደ​ረገ የለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos