2 ዜና መዋዕል 19:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባለ ራእዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፥ ንጉሡንም ኢዮሣፍጥን እንዲህ አለው፦ “ከሐዲውን ታግዛለህን? ወይስ ጌታን የሚጠሉትን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከጌታ ዘንድ ቁጣ ሆኖብሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባለራእዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሥ ኢዮሣፍጥንም እንዲህ አለው፣ “አንተ ክፉውን መርዳትህና እግዚአብሔርን የሚጠሉትን ማፍቀርህ ተገቢ ነውን? ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ ባንተ ላይ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሐናኒ ልጅ የሆነው ኢዩ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ለመገናኘት መጥቶ እንዲህ ሲል ገሠጸው፤ “አንተ ክፉዎችን መርዳትና እግዚአብሔርን ከሚጠሉት ጋር መተባበር መልካም ይመስልሃልን? ይህ ያደረግኸው ክፉ ነገር የእግዚአብሔር ቊጣ በአንተ ላይ እንዲወርድ አድርጎአል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነቢዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሡንም ኢዮሣፍጥን፥ “ኀጢአተኛውን ታግዛለህን? ወይስ እግዚአብሔር የሚጠላውን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ቍጣ መጥቶብሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባለ ራእዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን “ከሐዲውን ታግዛለህን? ወይስ እግዚአብሔርን የሚጠሉትን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ቍጣ ሆኖብሃል። |
ጌታ በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባዕሻና በቤተሰቡ ላይ ያን የትንቢት ቃል የተናገረበት ምክንያት፥ ባዕሻ በፈጸመው ኃጢአት ጌታን ስላሳዘነ ነበር፤ ባዕሻ ጌታን ያስቆጣውም ከእርሱ ፊት የነበረው ንጉሥ ባደረገው ዓይነት ስለ ሠራው ክፉ ነገር ብቻ ሳይሆን የኢዮርብዓምንም ቤተሰብ ሁሉ በመግደሉ ጭምር ነው።
አንተም ቀድሞ እንደጠፋብህ ሠራዊት፥ ፈረሱን በፈረስ ፋንታ፥ ሠረገላውንም በሠረገላ ፋንታ፥ ሠራዊትን ቁጠር፥ በሜዳም ላይ ከእነርሱ ጋር እንዋጋለን፥ በእርግጥም እንበረታባቸዋለን።” ምክራቸውንም ሰማ፥ እንዲሁም አደረገ።
በዚያን ጊዜም ባለ ራእዩ ዓናኒ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “በሶሪያ ንጉሥ ታምነሃልና፥ በአምላክህም በጌታ አልታመንህምና ስለዚህ የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት ከእጅህ አምልጦአል።
የእስራኤልም ንጉሥ አክዓብ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፦ “ከእኔ ጋር ወደ ሬማት ዘገለዓድ ትሄዳለህን?” አለው። እርሱም፦ “እኔ እንደ አንተ ነኝ፥ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ ናቸው፤ በጦርነቱም ላይ ከአንተ ጋር እንሆናለን” ብሎ መለሰለት።
የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን እንዲህ አለው፦ “ጌታን የምንጠይቅበት አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ ስለ እኔ ክፉ እንጂ ከቶ መልካም ትንቢት አይናገርምና እጠላዋለሁ፤ እርሱም የይምላ ልጅ ሚክያስ ነው።” ኢዮሣፍጥም፦ “ንጉሡ እንዲህ አይበል” አለው።
በከተሞቻቸውም ከተቀመጡት ከወንድሞቻቸሁ ዘንድ ስለ ደም መፋሰስ ስለ ሕግና ስለ ትእዛዝ ስለ ሥርዓትና ስለ ፍርድም ማናቸውም ጉዳይ ወደ እናንተ ቢመጣ ጌታን እንዳይበድሉ፥ ቁጣም በእናንተና በወንድሞቻችሁ ላይ እንዳይመጣ አስጠንቅቁአቸው፤ እንዲህም ብታደርጉ በደለኞች አትሆኑም።
የአባቶቻቸውንም አምላክ ጌታን ትተው የማምለኪያ ዐፀዶችንና ጣዖታትን አመለኩ፤ በዚህ በደላቸውም ምክንያት በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ቁጣ ወረደ።
ንጉሡንም ዖዝያንን እየተቃወሙ እንዲህ አሉት፦ “ዖዝያን ሆይ! ዕጣን ማጠን የተቀደሱት የአሮን ልጆች የካህናቱ ሹመት ነው እንጂ ለጌታ እንድታጥን ለአንተ አይገባህም፤ በድለሃልና ከመቅደሱ ውጣ፤ ከአምላክህም ከጌታ ዘንድ ክብር አያስገኝልህም።”
አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም፤ እኔ ጌታ አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥
አሞጽም ለአሜስያስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፦ እኔ የመንጋዎች ጠባቂና የወርካ ዛፎችን ተንከባካቢ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም፤
“እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉ ሞት ይገባቸዋል” የሚለውን ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ሕግ ቢያውቁም፥ እነዚህን ነገሮች ማድረግ ብቻ ሳይሆን፥ እንዲህ የሚያደርጉትንም ያበረታታሉ።
በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነኝና አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም።
አመንዝሮች ሆይ! ከዓለም ጋር ወዳጅ መሆን የእግዚአብሔር ጠላትነት መሆኑን አታውቁምን? ስለዚህ የዓለም ወዳጅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።
ቀደም ሲል በእስራኤል ዘንድ አንድ ሰው እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሲሄድ፥ “ኑ፥ ወደ ባለ ራእዩ እንሂድ” ይል ነበር፤ ዛሬ ነቢይ የሚባለው በዚያ ጊዜ ባለ ራእይ ይባል ነበርና።