Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 71:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 መዘርዘር ከምችለው በላይ ቢሆንም፥ አፌ ጽድቅህን ሁልጊዜም ማዳንህን ይናገራል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 አንደበቴ ስለ ጽድቅህ፣ ቀኑን ሙሉ ስለ ማዳንህ ይናገራል፤ ማቆሚያ ልኩንም አላውቅም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ምንም እንኳ ማስተዋል ቢያዳግተኝ፥ አንደበቴ ስለ ትክክለኛ ፍርድህና ስለ አዳኝነትህ ቀኑን ሙሉ ይናገራል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እርሱ ይኖ​ራል፥ ከዓ​ረ​ብም ወር​ቅን ይሰ​ጡ​ታል፤ ሁል​ጊ​ዜም ስለ እርሱ ይጸ​ል​ያሉ፥ ዘወ​ት​ርም ይመ​ር​ቁ​ታል።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 71:15
18 Referencias Cruzadas  

ጌታን የታመነ ወደ ትዕቢተኛና ወደ ሐሰተኛ ያልተመለከተ ሰው ብፁዕ ነው።


ምላሴ ጽድቅህን ሁልጊዜም ምስጋናህን ይናገራል።


በየቀኑ ሁሉ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም ለዘለዓለም ዓለምም አመሰግናለሁ።


አፌን ምስጋና ሞላ ሁልጊዜ ክብርህንና እዘምር ዘንድ።


እልልታ የሚያውቅ ሕዝብ ብፁዕ ነው፥ አቤቱ፥ በፊትህ ብርሃን ይሄዳሉ።


ጉዳቴን የሚሹ ባፈሩና በተነወሩ ጊዜ አንደበቴ ደግሞ ሁልጊዜ ጽድቅህን ይናገራል።


ልቅሶዬን ወደ እልልታ ለወጥህልኝ፥ ማቄን ቀድደህ ደስታንም አስታጠቅኸኝ።


አቤቱ፥ አንተ ርኅራኄህን ከእኔ አታርቅ፥ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ።


በማጠጫው መካከል ካሉት ከቀስተኞች ጩኸት ርቀው፥ በዚያ የጌታን ጽድቅ፥ በእስራኤል ላይ የግዛቱን ጽድቅ ይጫወታሉ፥ ከዚያም በኋላ የጌታ ሕዝብ ወደ በሮች ወረዱ።


ምድር ሁሉ ጌታን አመስግኑ፤ ዕለት ዕለት ማዳኑን አውሩ።


አቤቱ አምላኬ፥ ያደረግኸው ተአምራት ብዙ ነው፥ አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፥ ባወራም ብናገርም ከቍጥር ሁሉ በዛ።


የመድኃኒቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከደም አድነኝ፥ አንደበቴም በአንተ ጽድቅ ትደሰታለች።


ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፥ መጠለያዬም ጌታ ነው ሥራህን ሁሉ እናገር ዘንድ።


ጥንቃቄን ትጠብቅ ዘንድ ከንፈሮችህም እውቀትን እንዲጠብቁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios