1 ሳሙኤል 21:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም፥ “ሰው ሁሉ የሚበላው እንጀራ የለኝም፤ ነገር ግን ሰዎቹ በቅርቡ ከሴት የተጠበቁ ከሆነ፥ የተቀደሰ እንጀራ በዚህ አለ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም ዳዊትን፣ “ሰው ሁሉ የሚበላው እንጀራ የለኝም፤ ነገር ግን ሰዎቹ በቅርቡ ከሴት የተጠበቁ ከሆነ፣ የተቀደሰ እንጀራ በዚህ አለ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም “ከተቀደሰው ኅብስት በቀር ሕዝብ የሚመገበው እንጀራ የለኝም፤ ተከታዮችህ በቅርቡ ከሴቶች ጋር ሳይገናኙ ተቈጥበው በንጽሕና የቈዩ ከሆኑ፥ ይህን ኅብስት መብላት ይችላሉ” ሲል መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ለዳዊት መልሶ፥ “ሁሉ የሚበላው እንጀራ የለኝም፤ ነገር ግን የተቀደሰ እንጀራ አለ፤ ብላቴኖቹ ከሴቶች ንጹሓን እንደ ሆኑ መብላት ይችላሉ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ለዳዊት መልሶ፦ ሁሉ የሚበላው እንጀራ የለኝም፥ ነገር ግን የተቀደስ እንጀራ አለ፥ ብላቴኖቹ ከሴቶቹ ንጹሐን እንደ ሆኑ መብላት ይቻላል አለው። |
ለሠራዊት ጌታ ቤት ካህናት ለነቢያትም፦ “ለብዙ ዓመታት እንዳደረግሁት በአምስተኛው ወር መጾምና ማልቀስ ይገባኛልን?” ብለው እንዲናገሩ ልኳቸው ነበር።
ለጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ እንዲሁም ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ አብራችሁ ሁኑ።
ስለዚህ ካህኑ የተቀደሰውን እንጀራ ለዳዊት ሰጠው፤ ከጌታ ፊት ተነሥቶ በትኩስ እንጀራ ከተተካው ከኅብስት በስተቀር በዚያ ሌላ እንጀራ አልነበረምና።