1 ዜና መዋዕል 2:54 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰልሞንም ልጆች ቤተልሔም፥ ነጦፋውያን፥ ዓጣሮት-ቤት-ዮአብ፥ የመናሕታውያን እኩሌታ፥ ጾርዓውያን ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰልሞን ዘሮች፤ ቤተ ልሔም፣ ነጦፋውያን፣ ዓጣሮት ቤት ዮአብ፣ የመናሕታውያን እኩሌታ፣ ጾርዓውያን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሳልማ ልጆች ቤተልሔም፥ ነጦፋውያን፥ ዐጣሮት ቤት ዮአብ፥ የመናሐታውያን እኩሌታና ጾርዓውያን ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰልሞንም ልጆች ቤተ ልሔም፥ ነጦፋውያን፥ አጦሮት ቤትዮአብ፥ የመናሕታውያን እኩሌታ፥ ሰራዓውያንም ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰልሞንም ልጆች ቤተ ልሔም፥ ነጦፋውያን፥ ዓጣሮትቤትዮአብ፥ የመናሕታውያን እኵሌታ፥ ጾርዓውያን ነበሩ። |
በያቤጽም የተቀመጡ የጸሐፊዎች ወገኖች፤ ቲርዓውያን፥ ሺምዓታውያን፥ ሡካታውያን ነበሩ፤ እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የወጡ ቄናውያን ናቸው።
መሳፍንት ይፈርዱ በነበረበት ዘመን በአገሩ ላይ ረሀብ ሆነ። አንድ ሰውም ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር በሞዓብ ምድር ለመቀመጥ ከቤተልሔም ይሁዳ ተነሥቶ ሄደ።