በዚያም ቀን በታላቅ ደስታ በእግዚአብሔር ፊት በሉ፥ ጠጡም። የዳዊትንም ልጅ ሰሎሞንን ሁለተኛ ጊዜ አነገሡት፤ እርሱንም ንጉሥ ይሆን ዘንድ ለእግዚአብሔር ቀቡት፤ ሳዶቅም በካህናት ላይ ተሾመ።
ዘካርያስ 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምትበሉበትና በምትጠጡበትስ ጊዜ፥ ለራሳችሁ የምትበሉና የምትጠጡ አይደላችሁምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትበሉና ትጠጡ የነበረውስ ለራሳችሁ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስትበሉና ስትጠጡስ፥ የምትበሉትና የምትጠጡት ለራሳችሁ አይደለምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምትበሉበትና በምትጠጡበትስ ጊዜ የምትበሉትና የምትጠጡት ለራሳችሁ ብቻ አልነበረምን?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምትበሉበትና በምትጠጡበትስ ጊዜ፥ ለራሳችሁ የምትበሉና የምትጠጡ አይደላችሁምን? |
በዚያም ቀን በታላቅ ደስታ በእግዚአብሔር ፊት በሉ፥ ጠጡም። የዳዊትንም ልጅ ሰሎሞንን ሁለተኛ ጊዜ አነገሡት፤ እርሱንም ንጉሥ ይሆን ዘንድ ለእግዚአብሔር ቀቡት፤ ሳዶቅም በካህናት ላይ ተሾመ።
ለሚቃጠል መሥዋዕት በጎችህን አላቀረብህልኝም፤ በሌላም በሚቃጠል መሥዋዕትህ አላከበርኸኝም፤ በእህልም ቍርባን አላስቸገርሁህም፤ በዕጣንም አላደከምሁህም።
“ስለ ምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅኸንም?” ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።
መሥዋዕትንም ቢሠዉ፥ ሥጋንም ቢበሉ፤ እግዚአብሔር አይቀበላቸውም፤ አሁንም በደላቸውን ያስባል፤ በኀጢአታቸውም ይበቀላቸዋል፤ እነርሱም ወደ ግብፅ ይመለሳሉ፤ በአሦርም ርኩስ ነገርን ይበላሉ።
ለእግዚአብሔርም የወይን ጠጅን ቍርባን አያቀርቡም፤ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘውም፤ እንደ ኀዘንም እንጀራ ይሆንባቸዋል፤ የሚበላውም ሁሉ ይረክሳል፤ እንጀራቸውም ለሰውነታቸው ይሆናል እንጂ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይገባም።
ለምድሩ ሕዝብ ሁሉ ለካህናትም እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር በጾማችሁና ባለቀሳችሁ ጊዜ፥ በውኑ ለእኔ ጾም ጾማችሁልኝ?
ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች ገና ሰዎች ባሉባቸው ጊዜ፥ በምቾትም ተቀምጠው ሳሉ፥ ደቡቡና ቈላውም ሰዎች ባሉባቸው ጊዜ፥ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት እጅ የተናገረውን ቃል መስማት አይገባችሁምን?
በዚያም በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ብሉ፤ እጃችሁንም በምትዘረጉበት፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር በባረካችሁ ነገር ሁሉ፥ እናንተና ቤተሰባችሁ ደስ ይበላችሁ።
በዚያም በብሩ ሰውነትህ የፈለገውን፥ በሬ ወይም በግ፥ ወይም የወይን ጠጅ፥ ወይም ብርቱ መጠጥ፥ ሰውነትህ የሚሻውን ሁሉ ትገዛለህ፤ በዚያም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ትበላዋለህ፤ አንተና ቤተ ሰብህም ደስ ይላችኋል።
በቃልም ቢሆን፥ ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አድርጉ፤ ስለ እርሱም እግዚአብሔር አብን አመስግኑት።
እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፥ “ፊቱን፥ የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንደሚያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።