Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘካርያስ 7:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ስትበሉና ስትጠጡስ፥ የምትበሉትና የምትጠጡት ለራሳችሁ አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ትበሉና ትጠጡ የነበረውስ ለራሳችሁ አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በምትበሉበትና በምትጠጡበትስ ጊዜ የምትበሉትና የምትጠጡት ለራሳችሁ ብቻ አልነበረምን?”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በምትበሉበትና በምትጠጡበትስ ጊዜ፥ ለራሳችሁ የምትበሉና የምትጠጡ አይደላችሁምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በምትበሉበትና በምትጠጡበትስ ጊዜ፥ ለራሳችሁ የምትበሉና የምትጠጡ አይደላችሁምን?

Ver Capítulo Copiar




ዘካርያስ 7:6
15 Referencias Cruzadas  

በዚያም ቀን በታላቅ ደስታ በጌታ ፊት በሉ ጠጡም። የዳዊትንም ልጅ ሰሎሞንን ሁለተኛ ጊዜ አነገሡት፤ እርሱንም ልዑል እንዲሆን ለጌታ ቀቡት፥ ሳዶቅንም ካህን እንዲሆን ቀቡት።


ለሚቃጠል መሥዋዕት በጎችህን አላቀረብህልኝም፤ በሌላም መሥዋዕትህ አላከበርኸኝም፤ በእህልም ቁርባን አላስቸገርሁህም፤ በዕጣንም አላደከምሁህም።


“ስለምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም?” ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።


የተመረጠውን መሥዋዕቴን ያቀርባሉ፥ ሥጋንም ያርዳሉ፥ ይበላሉም፤ ጌታ ግን በእነርሱ ደስ አይሰኝም፤ በደላቸውን አሁን ያስታውሳል፥ ስለ ኃጢአታቸውም ይቀጣቸዋል፤ እነርሱም ወደ ግብጽ ይመለሳሉ።


ለጌታም የወይን ጠጅን ቁርባን አያፈስሱም፥ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘውም፤ እንደ ኀዘን እንጀራም ይሆንባቸዋል፥ የሚበሉትም ሁሉ ይረክሳሉ፤ እንጀራቸውም ለሆዳቸው ይሆናል እንጂ ወደ ጌታ ቤት አይገባም።


ለምድሩ ሕዝብና ለካህናት ለሁሉም እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር ስትጾሙና ስታለቅሱ፥ በውኑ ለእኔ ነው የጾማችሁልኝ?


ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች ገና ሰዎች እየኖሩባቸው፥ በሰላም ተቀምጠው እያሉ፥ ደቡቡና ቈላውም ሰዎች እየኖሩባቸው በነበረ ጊዜ አይደለም እንዴ፥ ይህንን ቃል ጌታ በቀደሙት ነቢያት አማካኝነት የተናገረው?


እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ ወይም ማናቸውንም ነገር ስታደርጉ፥ ሁሉን ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።


በዚያም በጌታ በአምላካችሁ ፊት ትበላላችሁ፤ ጌታ አምላካችሁ እናንተን በባረከበት፥ በምታደርጉት ሁሉ አንተና ቤተሰቦችህ ሐሤት ታደርጋላችሁ።”


በብሩም ደስ ያለህን ሁሉ ማለትም በሬና በግ፥ የወይን ወይም የብርቱ መጠጥ ወይም የምትሻውን ሁሉ ግዛበት። ከዚያም አንተና ቤተሰብህ በጌታህ በእግዚአብሔር ፊት ትበላዋለህ፤ አንተና ቤተሰብህም ሐሤትም ታደርጋላችሁ።


በኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።


ጌታ ግን ሳሙኤልን፥ “መልኩን ወይም ቁመቱን አትይ፤ እኔ ንቄዋለሁና። ጌታ የሚያየው፥ ሰው እንደሚያየው አይደለም። ሰው የውጭውን ገጽታ ያያል፤ ጌታ ግን ልብን ያያል” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos