እግዚአብሔርንም አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ፥ ዕለት ዕለትም ማዳኑን አውሩ።
ምስጋና ይዘን ፊቱ እንቅረብ፤ በዝማሬም እናወድሰው።
በምስጋና ወደ ፊቱ እንድረስ፥ በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል፥
ወደ ፊቱ ቀርበን እናመስግነው፤ በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል!
እዘምራለሁ፥ ንጹሕ መንገድንም አስተውላለሁ፤ ወደ እኔ መቼ ትመጣለህ? በቤቴ መካከል በልቤ ቅንነት እሄዳለሁ።
ጠማማ ልብም አልተከተለኝም፤ ክፉ ከእኔ በራቀ ጊዜ አላወቅሁም።
የእግዚአብሔርን ኀይል ማን ይናገራል? ምስጋናውንስ ሁሉ ይሰማ ዘንድ ማን ያደርጋል?
እግዚአብሔርም በሰማያት አንጐደጐደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ።
የአሕዛብም ጉባኤ ይከብብሃል፤ ስለዚህም ወደ አርያም ተመለስ።
እስከ መቼ ዐመፃን ትፈርዳላችሁ? እስከ መቼስ ለኀጢአተኞች ፊት ታደላላችሁ?
ክቡር ንጉሥ ፍርድን ይወድዳል፤ አንተ በኀይልህ ጽድቅን አጸናህ፥ ለያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ አደረግህ።
ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን?
መዝሙርንና ምስጋናን፥ የተቀደሰ ማሕሌትንም አንብቡ፤ በልባችሁም ለእግዚአብሔር ተቀኙ፤ ዘምሩም።
ከእናንተ መከራን የሚቀበል ማንም ቢኖር እርሱ ይጸልይ፤ ደስ የሚለውም ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር።