ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፥ “በእንግድነት የኖርሁት የሕይወቴ ዘመንስ መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፤ የሕይወቴም ዘመኖች ጥቂትም ክፉም ሆኑብኝ፤ አባቶች በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም።”
መዝሙር 90:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዕድሜያችን ዘመን ሰባ ዓመት፣ ቢበዛም ሰማንያ ነው፤ ከዚያ በላይ ከሆነም ድካምና መከራ ብቻ ነው፤ ቶሎ ያልፋልና፤ እኛም ወዲያው እንነጕዳለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት፥ ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው፥ ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው፥ ከእኛ ቶሎ ያልፋልና፥ እኛም እንጠፋለንና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕድሜአችን ሰባ ዓመት ነው፤ ቢበዛም ሰማኒያ ዓመት ነው፤ እነዚያም ዘመናት በችግርና በሐዘን የተሞሉ ናቸው፤ ዕድሜአችን በቶሎ ያልቃል፤ እኛም እናልፋለን። |
ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፥ “በእንግድነት የኖርሁት የሕይወቴ ዘመንስ መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፤ የሕይወቴም ዘመኖች ጥቂትም ክፉም ሆኑብኝ፤ አባቶች በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም።”
እግዚአብሔርም፥ “መንፈሴ በሰው ላይ ለዘለዓለም አይኖርም፤ እነርሱ ሥጋ ናቸውና፤ ዘመናቸውም መቶ ሃያ ዓመት ይሆናል” አለ።
ዛሬ የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነኝ፥ መልካሙንና ክፉውን መለየት እችላለሁን? እኔ ባሪያህ የምበላውንና የምጠጣውን ጣዕሙን መለየት እችላለሁን? የወንዱንና የሴቲቱን ዘፈን ድምፅ መስማትስ እችላለሁን? እኔ ባሪያህ በጌታዬ በንጉሡ ላይ ለምን እከብድብሃለሁ?
ከፍ ከፍ ባለ ጊዜም ብዙዎችን አስጨነቃቸው። እንደ አመድማዶ በሙቀት ይጠወልጋል። ከቃርሚያው እንደሚወድቅ እሸትም ይቈረጣል።
የቀረውንም ኑሬዬን አጣሁ። ከእኔም ወጣች፥ ተለየችም። ድንኳኑን ተክሎ እንደሚያድርና እንደሚሄድ፥ ሊቈረጥ እንደ ተቃረበ ሸማም እንዲሁ ነፍሴ በላዬ ሆነች።
እግዚአብሔርም፦ አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍስህን ከሥጋህ ለይተው ይወስዷታል፤ እንግዲህ ያጠራቀምኸው ለማን ይሆናል? አለው።