መዝሙር 77:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀን በደመና መራቸው፥ ሌሊቱንም ሁሉ በእሳት ብርሃን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ነህ፤ በሕዝቦችም መካከል ኀይልህን ትገልጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ መንገድህ በመቅደስ ውስጥ ነው፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተአምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ነህ፤ አንተ በሕዝቦች መካከል ኀይልህን አሳይተሃል። |
እንዲህም ይሆናል፤ ከዚህ በኋላ ልጅህ፦ ‘ይህ ምንድን ነው?’ ብሎ በጠየቀህ ጊዜ እንዲህ ትለዋለህ፦ እግዚአብሔር በብርቱ እጅ ከባርነት ቤት ከግብፅ ምድር አወጣን፤
አቤቱ፦ በአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማን ነው? በምስጋና የተደነቅህ ነህ፤ ድንቅንም የምታደርግ ነህ፤
እግዚአብሔር የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፤ በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን ማዳን ያያሉ።
“ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ! የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፤ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ፤” እያሉ የእግዚአብሔርን ባሪያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።