ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥ ዐመፃን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ለኀጢአት ምክንያት እንዳልሰጥ፤ ከምርጦቻቸውም ጋር አልተባበር።
መዝሙር 58:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም አቤቱ፥ የኀያላን አምላክ፥ የእስራኤል ንጉሥ፥ አሕዛብን ሁሉ ጐብኛቸው፥ ይቅርም በላቸው፤ ዐመፅ የሚያደርጉትን ሁሉ ግን አትማራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጆሮዋንም የደፈነችው የመተተኛውን ወይም የጠቢቡን ደጋሚ ቃል ላለመስማት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእባብ መርዝ ዓይነት መርዝ አላቸው፥ ጆሮውን እንደደፈነ እባብ ናቸው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እፉኝት ጆሮውን የሚደፍነው የእባብ አፍዛዦችን ድምፅ፥ ወይም የአስማተኞችን ድግምት ላለመስማት ነው። |
ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥ ዐመፃን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ለኀጢአት ምክንያት እንዳልሰጥ፤ ከምርጦቻቸውም ጋር አልተባበር።
የግብፅም መንፈስ በውስጣቸው ትደነግጣለች፤ ምክራቸውን አጠፋለሁ፤ እነርሱም አማልክቶቻቸውንና ጣዖቶቻቸውን፥ ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎቻቸውንም ይጠይቃሉ።
እነሆ አስማት የማይከለክላቸውን የሚገድሉ እባቦችን እሰድድባችኋለሁ፤ እነርሱም ይነድፉአችኋል፥” ይላል እግዚአብሔር።
በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም፥ በወፍም የሚያሟርት በአንተ ዘንድ አይገኝ።