መዝሙር 50:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ከንፈሮችን ክፈት፥ አፌም ምስጋናህን ያወራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመከራ ጊዜ ወደ እኔ ጩኽ፤ አድንሃለሁ፤ አንተም ታከብረኛለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመከራ ቀን ጥራኝ፥ አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መከራ በሚደርስብህ ጊዜ ጥራኝ፤ እኔም አድንሃለሁ፤ አንተም ታከብረኛለህ።” |
እንዲህም አሉ፦ ክፉ ነገር፥ የፍርድ ሰይፍ ወይም ቸነፈር ወይም ራብ፥ ቢመጣብን በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ እንቆማለን፤ ስምህ በዚህ ቤት ላይ ነውና፤ በመከራችንም ወደ አንተ እንጮኻለን፥ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ።
እናንት የሰው ልጆች፥ እስከ መቼ ድረስ ልባችሁን ታከብዳላችሁ? ከንቱ ነገርን ለምን ትወድዳላችሁ? ሐሰትንም ለምን ትሻላችሁ?
ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።
ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ “እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኀይል ነው” ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።
እግዚአብሔርም የዚያችን የአህያ መንጋጋ አጥንት ስንጥቃት ከፈተ፤ ከእርስዋም ውኃ ወጣ፤ እርሱም ጠጣ፤ ነፍሱም ተመለሰች፤ ከውኃ ጥሙም ዐረፈ። ስለዚህም የዚያ ቦታ ስም እስከ ዛሬ ድረስ “ነቅዐ አጽመ መንሰክ” ተብሎ ተጠራ።