La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 34:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፈተ​ኑኝ፥ በእኔ ላይም ዘበ​ቱ​ብኝ፥ ሣቁ​ብ​ኝም፤ ጥር​ሳ​ቸ​ው​ንም በእኔ ላይ አን​ቀ​ጫ​ቀጩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእግዚአብሔር ፊት ግን፣ መታሰቢያቸውን ከምድር ለማጥፋት በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮዎቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ክፉ አድራጊዎችን ግን ይቃወማል፤ መታሰቢያቸውንም ከምድር ላይ ያጠፋል።

Ver Capítulo



መዝሙር 34:16
15 Referencias Cruzadas  

መታ​ሰ​ቢ​ያ​ውም ከም​ድር ይጠ​ፋል፤ በም​ድ​ርም ስም አይ​ቀ​ር​ለ​ትም።


ዐይ​ኑን ከጻ​ድ​ቃን ላይ አያ​ር​ቅም፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ከነ​ገ​ሥ​ታት ጋር በዙ​ፋን ላይ ያስ​ቀ​ም​ጣ​ቸ​ዋል፥ በድል አድ​ራ​ጊ​ነ​ትም ያኖ​ራ​ቸ​ዋል። እነ​ር​ሱም ከፍ ከፍ ይላሉ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ንጹሕ ነው፤ ነፍ​ስ​ንም ይመ​ል​ሳል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክር የታ​መነ ነው፤ ሕፃ​ና​ት​ንም ጠቢ​ባን ያደ​ር​ጋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በል​ባ​ቸው የዋ​ሃን ለሆኑ ቅርብ ነው፥ በመ​ን​ፈስ ትሑ​ታን የሆ​ኑ​ት​ንም ያድ​ና​ቸ​ዋል።


የተ​ፈ​ታ​ተ​ኑኝ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ፈተ​ኑኝ፥ ሥራ​ዬ​ንም አዩ።


የጻድቃን መታሰቢያ ከምስጋና ጋር ነው። የኃጥኣን ስም ግን ይጠፋል።


እግዚአብሔር ከኃጥኣን ፈጽሞ ይርቃል፤ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል። ከዐመፃ ጋር ካለ ብዙ ሀብት ይልቅ፥ ከእውነት ጋር ያለ ጥቂት ሀብት ይሻላል። አካሄዱ ከእግዚአብሔር ይቃናለት ዘንድ፥ የደግ ሰው ልብ እውነትን ያስባል።


እን​ዲ​ሁም ያን​ጊዜ ኃጥ​ኣን ወደ ጽኑ መቃ​ብር ሲገቡ አየሁ፥ ከቅ​ድ​ስት ስፍ​ራም ወጥ​ተው ተለዩ፤ እነ​ር​ሱም በከ​ተ​ማዋ ተመ​ሰ​ገኑ፥ እን​ዲህ ሠር​ተ​ዋ​ልና፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።


አቤቱ! የእ​ስ​ራ​ኤል ተስፋ ሆይ! የሚ​ተ​ዉህ ሁሉ ያፍ​ራሉ፤ ከአ​ን​ተም የሚ​ለዩ የሕ​ይ​ወ​ትን ውኃ ምንጭ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተ​ዋ​ልና በም​ድር ላይ ይጻ​ፋሉ።


“ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይሁ​ዳን ሁሉ አጠፋ ዘንድ፥ ፊቴን ለክ​ፋት በላ​ያ​ችሁ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


“ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ ወይም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚ​በ​ላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከ​ብ​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ ያንም ሰው ከሕ​ዝቡ ለይች አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ።


ፊቴ​ንም አከ​ብ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ፊት ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁም ያሸ​ን​ፉ​አ​ች​ኋል። ማንም ሳያ​ሳ​ድ​ዳ​ችሁ ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ።


በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ፊት ተማ​ር​ከው ቢሄዱ በዚያ ሰይ​ፍን አዝ​ዛ​ታ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋም ትገ​ድ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ ዐይ​ኔ​ንም ለመ​ል​ካም ሳይ​ሆን ለክ​ፋት በእ​ነ​ርሱ ላይ እጥ​ላ​ለሁ።”