La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 12:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እስከ መቼ በነ​ፍሴ ኀዘ​ንን አኖ​ራ​ለሁ? እስከ መቼ ልቤ ሁል​ጊዜ ትጨ​ነ​ቅ​ብ​ኛ​ለች? እስከ መቼ ጠላ​ቶች በላዬ ይታ​በ​ያሉ?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤ በሽንገላ ከንፈርና በሁለት ልብ ይናገራሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንዱ ለአንዱ ውሸትን ይናገራል፤ በሚያቈላምጥ አንደበት የሚናገሩትም በሁለት ልብ ነው።

Ver Capítulo



መዝሙር 12:2
25 Referencias Cruzadas  

በጭ​ፍ​ራ​ውም ውስጥ ዳዊ​ትን ለመ​ር​ዳት የወጡ የተ​ዘ​ጋጁ፥ መሣ​ሪ​ያም ሁሉ የያዙ የዛ​ብ​ሎን ሰዎች አምሳ ሺህ ነበሩ፤ ከእ​ነ​ርሱ አን​ድስ እንኳ ደካማ አል​ነ​በ​ረም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነውና፥ ጽድ​ቅ​ንም ይወ​ድ​ዳል፤ ቅን​ነት ግን ፊቱን ታየ​ዋ​ለች።


“ለመ​ን​ግ​ሥ​ትህ ክብር ይገ​ባል” ይላሉ፥ ኀይ​ል​ህ​ንም ይነ​ጋ​ገ​ራሉ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ባይና መሓሪ ነው፥ መዐቱ የራቀ፥ ምሕ​ረቱ የበዛ እው​ነ​ተኛ ነው፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በው​ኆች ላይ ነው። የክ​ብር አም​ላክ አን​ጐ​ደ​ጐደ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብዙ ውኆች ላይ ነው።


አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን ስማ፥ ልመ​ና​ዬ​ንም አድ​ምጥ፥ ልቅ​ሶ​ዬ​ንም አድ​ምጥ፥ ቸልም አት​በ​ለኝ፤ እኔ በም​ድር ላይ መጻ​ተኛ ነኝና፥ እንደ አባ​ቶ​ችም ሁሉ እን​ግዳ ነኝና።


ነፍሴ በእኔ ውስጥ ታወ​ከች፤ ስለ​ዚህ አቤቱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ምድር፥ በአ​ር​ሞ​ን​ኤ​ምም በታ​ናሹ ተራራ አስ​ብ​ሃ​ለሁ።


በአ​ፋ​ቸው እው​ነት የለ​ምና፥ ልባ​ቸ​ውም ከንቱ ነው፥ ጕሮ​ሮ​ኣ​ቸው እንደ ተከ​ፈተ መቃ​ብር ነው፤ በም​ላ​ሳ​ቸው ይሸ​ነ​ግ​ላሉ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይ​ልን እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ እር​ሱም የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​ንን ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል።


እን​ዲህ በሕ​ይ​ወቴ ዘመን አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥ በአ​ን​ተም ስም እጆ​ችን አነ​ሣ​ለሁ።


ዘዋሪ ሐሜተኛ ምሥጢርን ይገልጣል፤ በከንፈሩ የሚያባብል ሰውን አትገናኘው።


ይቅር ባይ ሰው ታላቅና ክቡር ነው፤ ነገር ግን የታመነ ሰው የሚገኘው በድካም ነው።


አን​ተም፦ የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ያል​ሰማ፥ ተግ​ሣ​ጽ​ንም ያል​ተ​ቀ​በለ ሕዝብ ይህ ነው፤ እው​ነት ጠፍ​ቶ​አል፤ ከአ​ፋ​ቸ​ውም ተቈ​ር​ጦ​አል ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።


ምላ​ሳ​ቸው የተ​ሳለ ፍላጻ ነው፤ ንግ​ግ​ራ​ቸው ሽን​ገላ ነው፤ ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ቸው ሰላ​ምን ይና​ገ​ራሉ፤ በል​ባ​ቸው ግን ጥላ​ቻን ይይ​ዛሉ።


ከዚ​ህም በኋላ በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት መካ​ከል ከንቱ ራእ​ይና ውሸ​ተኛ ምዋ​ርት አይ​ሆ​ንም።


ደግ ሰው ከምድር ጠፍቶአል፥ በሰውም መካከል ቅን የለም፥ ሁሉ ደምን ለማፍሰስ ያደባሉ፥ ሰውም ሁሉ ወንድሙን በመረብ ለመያዝ ይከታተለዋል።


እነ​ርሱ ለጌ​ታ​ችን ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያይ​ደለ ለሆ​ዳ​ቸው ይገ​ዛ​ሉና፤ በነ​ገር ማታ​ለ​ልና በማ​ለ​ዛ​ዘ​ብም የብ​ዙ​ዎች የዋ​ሃ​ንን ልብ ያስ​ታሉ፤


እንደምታውቁ፥ እያቈላመጥን ከቶ አልተናገርንም፤ እግዚአብሔርም እንደሚመሰክር እያመካኘን በመጐምጀት አልሠራንም፤