እግዚአብሔርም አብራምን አለው፥ “ዘርህ ለእነርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ ዕወቅ፤ አራት መቶ ዓመታትም ባሪያዎች አድርገው ይገዙአቸዋል፤ ያሠቃዩአቸዋል፤ ያስጨንቋቸዋልም።
መዝሙር 105:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በድንኳኖቻቸውም ውስጥ አንጐራጐሩ፤ የእግዚአብሔርንም ቃል አልሰሙም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡን እንዲጠሉ፣ በባሪያዎቹም ላይ እንዲያሤሩ ልባቸውን ለወጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡን ይጠሉ ዘንድ በአገልጋዮቹም ላይ ተንኰል ይፈጽሙ ዘንድ ልባቸውን ለወጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ግን ወገኖቹን እንዲጠሉና፥ በአገልጋዮቹም ላይ በተንኰል እንዲነሡ ግብጻውያንን አስጨከነ። |
እግዚአብሔርም አብራምን አለው፥ “ዘርህ ለእነርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ ዕወቅ፤ አራት መቶ ዓመታትም ባሪያዎች አድርገው ይገዙአቸዋል፤ ያሠቃዩአቸዋል፤ ያስጨንቋቸዋልም።
“እናንተ ዕብራውያትን ሴቶች ስታዋልዱ ለመውለድ እንደ ደረሱ በአያችሁ ጊዜ፥ ወንድ ቢሆን ግደሉት፤ ሴት ብትሆን ግን አትግደሏት።”
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፥ “ወደ ፈርዖን ግባ፤ እኔ የፈርዖንንና የሹሞቹን ልብ አጽንቼአለሁና፥ ተአምራቴ በእነርሱ ላይ በትክክል ይመጣ ዘንድ፤
ከዚያም ከብዙ ቀን በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የግብፅ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ልጆች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፤ ጮኹም፤ ስለ ባርነታቸውም ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ግብፅ ተመልሰህ ስትሄድ በእጅህ ያደረግሁትን ተአምራቴን ሁሉ በፈርዖን ፊት ታደርገው ዘንድ ተመልከት፤ እኔ ግን ልቡን አጸናዋለሁ፤ ሕዝቡንም አይለቅቅም።
የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መንፈሱን አደንድኖታልና፥ ልቡንም አጽንቶታልና።