የይሁዳና የብንያም የአባቶች ቤቶች አለቆችም፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት ይወጡ ዘንድ እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣው ሁሉ ተነሡ።
መዝሙር 102:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍጥረታችንን እርሱ ያውቃልና፤ አቤቱ፥ እኛ አፈር እንደ ሆንን አስብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልጋዮችህ በድንጋዮቿ ደስ ይሰኛሉ፤ ለዐፈሯም ይሳሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ተነሥ ለጽዮንም ራራ፥ የጸጋዋ ጊዜ ነውና፥ ዘመንዋም ደርሶአልና፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድንጋዮችዋ በአገልጋዮችህ ዘንድ የተወደዱ ናቸው፤ ለፍርስራሾችዋ እንኳ ይራራሉ። |
የይሁዳና የብንያም የአባቶች ቤቶች አለቆችም፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት ይወጡ ዘንድ እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣው ሁሉ ተነሡ።
ያባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ያከብር ዘንድ ይህን ነገር በንጉሡ ልብ ያኖረ፥
እነርሱም፥ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ቅሬታዎች በታላቅ መከራና ስድብ አሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ።
እኔም፥ “እኛ ያለንበትን ጕስቍልና፥ ኢየሩሳሌም እንደ ፈረሰች፥ በሮችዋም በእሳት እንደ ተቃጠሉ ታያላችሁ። አሁንም ከእንግዲህ ወዲህ መሳለቂያ እንዳንሆን ኑና የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንሥራ” አልኋቸው።
ንጉሡንም፥ “ንጉሡ ለዘለዓለም ይኑር፤ የአባቶች መቃብር ያለባት ከተማ ተፈትታለችና፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋልና ፊቴ ስለ ምን አያዝን?” አልሁት።
በወንድሞቹና በሰማርያ ሠራዊትም ፊት፥ “ከተማቸውን የሚሠሩ እነዚህ ደካሞች አይሁድ ኀይላቸው ምንድን ነው? ይተዉላቸዋልን? ይሠዋሉን? በአንድ ቀንስ ይጨርሳሉን? የተቃጠለውንስ ድንጋይ ከፍርስራሹ መልሰው ያድኑታልን?” ብሎ ተናገረ።
እግዚአብሔርም ያዕቆብን ይምረዋል፤ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፤ በሀገራቸውም ያርፋሉ፤ መጻተኞችም ከእነርሱ ጋር አንድ ይሆናሉ፤ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጨመራሉ።
ካህናት ሆይ፥ ለኢየሩሳሌም ወደ ልቧ የሚገባ ነገርን ተናገሩ፤ ውርደቷ እንደ ተፈጸመ፥ ኀጢአቷም እንደ ተሰረየ፥ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች አጽናኑአት።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ደስ አሰኝሻለሁ፤ ባድማሽንም ሁሉ ደስ አሰኛለሁ፤ ምድረ በዳሽንም እንደ ዔድን፥ በረሃዎችሽንም እንደ እግዚአብሔር ገነት አደርጋለሁ። ደስታና ተድላ እምነትና የዝማሬ ድምፅ በውስጧ ይገኝባታል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፥ ወደዚህም ስፍራ እመልሳችሁ ዘንድ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፤ ለማደሪያውም እራራለሁ፤ ከተማዪቱም በጕብታዋ ላይ ትሠራለች፤ አዳራሹም እንደ ዱሮው የሰው መኖሪያ ይሆናል።
እርስዋም በሞዓብ ምድር ሳለች እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ ጐበኘ እንጀራም እንደ ሰጣቸው ስለ ሰማች፥ ከሞዓብ ምድር ልትመለስ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ተነሣች።