ምሳሌ 18:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኃጥኣንን ፊት ማድነቅ መልካም አይደለም። በፍርድ ጊዜም እውነትን ማራቅ መልካም አይደለም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለክፉ ሰው ማድላት፣ ንጹሑንም ፍትሕ መንሣት ተገቢ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጻድቅ ፍርድ ይጠምም ዘንድ፥ ለኀጥእም ማድላት መልካም አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለበደለኛው ማዳላትና ንጹሕ ሰው ትክክለኛ ፍትሕ እንዳያገኝ ማድረግ ተገቢ አይደለም። |
ፍርድን ከመከተል ወደ ኋላ ርቀናል፤ ጽድቅም በሩቅ ቆሞአል፤ እውነትም ከመንገዳቸው ታጥቶአል፤ በቀና መንገድም መሄድ አልቻሉም።
ደቀ ዛሙርታቸውንም ከሄሮድስ ወገን ጋር ላኩበት፤ እነርሱም “መምህር ሆይ! እውነተኛ እንደ ሆንህ በእውነትም የእግዚአብሔርን መንገድ እንድታስተምር እናውቃለን፤ ለማንምም አታደላም፤ የሰውን ፊት አትመለከትምና፤
ፍርድን አታጣምም፤ ፊት አይተህም አታድላ፤ ጉቦን አትቀበል፥ ጉቦ የጥበበኞችን ዐይን ያሳውራልና፥ የእውነትንም ቃል ያጣምማልና ጉቦ አትቀበል።