ከዚህም በኋላ አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው “በፊትህ የሄድሁ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መልካም አድርግ፤ ንጹሕም ሁን፤
ምሳሌ 18:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ስም ታላቅ ኀይል ነው፤ ጻድቃንም እርሱን በመከተል ከፍ ከፍ ይላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ በመሮጥ ተገን ያገኝበታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ስም የጸና ግምብ ነው፥ ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ስም እንደ ጠንካራ ምሽግ ነው፤ ስለዚህ ደጋግ ሰዎች ወደ እርሱ ተጠግተው ይድናሉ። |
ከዚህም በኋላ አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው “በፊትህ የሄድሁ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መልካም አድርግ፤ ንጹሕም ሁን፤
አቤቱ ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፤ መጥቶ እንዳያጠፋኝ፥ እናትን ከልጆችዋ ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና።
እግዚአብሔር ጠባቂዬ ነው፤ በእርሱም እታመናለሁ፤ ጋሻዬና የመድኀኒቴ ቀንድ፥ ረዳቴ፥ መጠጊያዬና መሸሸጊያዬ፥ መድኀኒቴ ሆይ፥ ከግፈኛ ታድነኛለህ።
አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ቸልም አትበለኝ። ቸል ብትለኝ ግን ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱት እሆናለሁ።
ለአብርሃምም፥ ለይስሐቅም፥ ለያዕቆብም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ፤ ነገር ግን ስሜ እግዚአብሔር አልታወቀላቸውም ነበር።
ለዘለዓለም በአርያም የሚኖር ስሙም ቅዱሰ ቅዱሳን የሆነ፥ በቅዱሳን አድሮ የሚኖር፥ ለተዋረዱት ትዕግሥትን የሚሰጥ፥ ልባቸውም ለተቀጠቀጠ ሕይወትን የሚሰጥ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፤
በዘመኑም ይሁዳ ይድናል፤ እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፤ ይህም ስም እግዚአብሔር በነቢያት ኢዮሴዴቅ ብሎ የጠራው ነው።
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፤ ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” የሚል ነው።
ዳዊትም ፍልስጥኤማዊዉን አለው፥ “አንተ ሰይፍና ጦር፥ ጋሻም ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን ዛሬ በተገዳደርኸው በእስራኤል ጭፍሮች አምላክ ስም በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ።
ስለ ወንዶችና ስለ ሴቶች ልጆቻቸውም የሕዝቡ ሁሉ ልብ አዝኖ ነበርና ሕዝቡ ሊወግሩት ስለ ተናገሩ ዳዊት እጅግ ተጨነቀ፤ ዳዊት ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ራሱን አጽናና።