ምሳሌ 11:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ጻድቅ በምድር ላይ በጭንቅ የሚድን ከሆነ፥ ይልቁንስ ኃጥእና ዐመፀኛ በወዴት ይገለጣሉ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጻድቅ በምድር የእጁን የሚያገኝ ከሆነ፣ ክፉውና ኀጢአተኛውማ የቱን ያህል የባሰ ያገኝ ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ ጻድቅ በምድር ላይ ፍዳውን የሚቀበል ከሆነ፥ ይልቁንስ ክፉዎችና ዓመፀኞችስ እንዴት ይሆኑ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደጋግ ሰዎች በምድር ላይ ሳሉ የመልካም ሥራቸውን ዋጋ ያገኛሉ፤ ክፉዎችና ኃጢአተኞች ግን እጅግ የበረታ ቅጣትን ይቀበላሉ። |
ተነሥቶም ሄደ፤ በመንገዱም ላይ አንበሳ አግኝቶ ገደለው፤ ሬሳውም በመንገድ ላይ ተጋድሞ ነበር፤ አህያውም በእርሱ አጠገብ ቆሞ ነበር፤ አንበሳውም ደግሞ በሬሳው አጠገብ ቆሞ ነበር።
በዓለም ሁሉ ላይ ክፋትን አዝዛለሁ፤ የኀጢአተኞችንም ኀጢአት እጐበኛለሁ፤ የትዕቢተኞችንም ኵራት እሽራለሁ፤ የጨካኞቹንም ኵራት አዋርዳለሁ።
እነሆ ስሜ የተጠራባትን ከተማ አስጨንቃት ዘንድ እጀምራለሁ፤ በውኑ እናንተ መንጻትን ትነጻላችሁን? በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ሰይፍን እጠራለሁና አትነጹም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ እስራኤልም በሳቱ ጊዜ ጣዖታቸውን ተከትለው ከእኔ ዘንድ የሳቱ ሌዋውያን ሳይቀር ኀጢአታቸውን ይሸከማሉ።