እግዚአብሔርም በባሪያዎቹ በነቢያት ሁሉ አፍ እንደ ተናገረው እስራኤልን ከፊቱ እስኪያወጣ ድረስ ከእርስዋ አልራቁም። እስራኤልም እስከ ዛሬ ድረስ ከምድሩ ወደ አሦር ፈለሰ።
ሚክያስ 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ በእግዚአብሔር ጉባኤ መካከል በዕጣ ገመድ የሚጥል አይኖርህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በእግዚአብሔር ጉባኤ ውስጥ፣ መሬት በዕጣ ገመድ የሚያካፍል ማንም አይኖርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በጌታ ጉባኤ መካከል በዕጣ ገመድ የሚጥል አይኖርህም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድሩ ተመልሶ ለእግዚአብሔር ሕዝብ በሚሰጥበት ጊዜ እናንተ ምንም ድርሻ አይኖራችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በእግዚአብሔር ጉባኤ መካከል በዕጣ ገመድ የሚጥል አይኖርህም። |
እግዚአብሔርም በባሪያዎቹ በነቢያት ሁሉ አፍ እንደ ተናገረው እስራኤልን ከፊቱ እስኪያወጣ ድረስ ከእርስዋ አልራቁም። እስራኤልም እስከ ዛሬ ድረስ ከምድሩ ወደ አሦር ፈለሰ።
ከቲልሜል፥ ከቲላሬስ፥ ከኪሩብ፥ ከአዶን፥ ከኢሜር የወጡ እነዚህ ናቸው፤ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ያስታውቁ ዘንድ አልቻሉም፤
ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፥ “እግዚአብሔር ለዘጠኙ ነገድና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ይሰጡአቸው ዘንድ እንደ አዘዘ በዕጣ የምትወርሱአት ምድር ይህች ናት፤
ልዑል አሕዛብን በከፈላቸው ጊዜ፥ የአዳምንም ልጆች በለያቸው ጊዜ፥ እንደ እግዚአብሔር መላእክት ቍጥር፥ አሕዛብን በየድንበራቸው አቆማቸው።
ከየነገዳችሁ ሁሉ ሦስት ሦስት ሰዎችን አምጡ፥ ተነሥተውም ሀገሪቱን ይዙሩአት፤ ለመክፈልም እንዲያመች ገልጠው ይጻፉአት፤ ወደ እኔም ይመለሳሉ።