ከሚንቀሳቀሱት ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩሳን የሚሆኑ እነዚህ ናቸው። ከእነርሱም በድናቸውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።
ዘሌዋውያን 11:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም በድናቸው በምንም ላይ ቢወድቅ እርሱ ርኩስ ነው፤ የዕንጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቍርበት ወይም ከረጢት ቢሆን የሚሠራበት ዕቃ ሁሉ እርሱን በውኃ ውስጥ ይንከሩት፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በድኑ በማንኛውም ዕቃ ላይ ቢወድቅ ያ ዕቃ ከዕንጨት፣ ከጨርቅ፣ ከቈዳ ወይም ከበርኖስ የተሠራ ከረጢት ቢሆን ርኩስ ይሆናል፤ በውሃ ውስጥ ይደረግ፤ ሆኖም ርኩስ ነው፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም የሞተው በማናቸውም ነገር ላይ ቢወድቅ እርሱ ርኩስ ይሆናል፤ የእንጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቆዳ ወይም ከረጢት ቢሆን ለማናቸውም ሥራ የሚጠቅም ዕቃ ሁሉ በውኃ ውስጥ ይደረግ፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ግን ይነጻል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በድናቸው የሚወድቅበት ነገር ሁሉ ይረክሳል፤ ይኸውም ከእንጨት የተሠሩ ዕቃዎችን፥ ልብስን፥ ቆዳን ወይም ከረጢት የመሳሰሉትንና ሌላውንም ነገር ሁሉ ይጨምራል፤ የእነርሱ በድን የነካው ይህን የመሰለ ዕቃ ሁሉ በውሃ ውስጥ ተነክሮ ይቈይ፤ እስከ ምሽትም ድረስ ርኩስ ሆኖ ከዚያ በኋላ ንጹሕ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም የሞተው በምንም ላይ ቢወድቅ እርሱ ርኩስ ነው፤ የእንጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቁርበት ወይም ከረጢት ቢሆን የሚሠራበት ዕቃ ሁሉ እርሱ በውኃ ውስጥ ይደረግ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል። |
ከሚንቀሳቀሱት ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩሳን የሚሆኑ እነዚህ ናቸው። ከእነርሱም በድናቸውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።
ካህኑም አንዲቱን ለኀጢአት መሥዋዕት፥ አንዲቱንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ሁሉ ያስተሰርይለታል።
ለመለቀቅ የሚሆነውን ፍየል የወሰደ ሰው ልብሱን ያጥባል፤ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገባል።
የሞተውን ወይም አውሬ የሰበረውን የሚበላ ሰው ሁሉ፥ የሀገር ልጅ ወይም እንግዳ ቢሆን፥ ልብሱን ያጥባል፤ በውኃም ይታጠባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።
ካህኑም ልብሱን ያጥባል፤ ገላውንም በውሃ ይታጠባል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገባል፤ ካህኑም እስከ ማታ ርኩስ ይሆናል።
መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤