ዮሐንስ 15:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተስ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ካደረጋችሁ ወዳጆች ናችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የማዝዛችሁን ብትፈጽሙ ወዳጆቼ ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተም እኔ የማዛችሁን ብትፈጽሙ ወዳጆቼ ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ። |
እግዚአብሔርንም ተከተለ፤ እርሱንም ከመከተል አልራቀም፤ እግዚአብሔርም ለሙሴ ያዘዘውን ትእዛዛቱን ጠበቀ።
አምላካችን ሆይ፥ በዚህ ምድር የነበሩትን አሕዛብ ከሕዝብህ ከእስራኤል ፊት ያሳደድህ፥ ለወዳጅህም ለአብርሃም ዘር ለዘለዓለም የሰጠሃት አንተ አይደለህምን?
እኅቴ ሙሽሪት ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከርቤዬን ከሽቱዬ ጋር ለቀምሁ፥ እንጀራዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወይን ጠጄን ከወተቴ ጋር ጠጣሁ። ባልንጀሮች በሉ፥ ጠገቡም፤ የወንድሞች ልጆች ጠጡ፥ ሰከሩም፥ ልባቸው የጠፋ ነውና።
እነርሱም ገብተው ወረሱአት፤ ነገር ግን ቃልህን አልሰሙም፤ በሕግህም አልሄዱም፤ ያደርጉም ዘንድ ካዘዝሃቸው ሁሉ ምንም አላደረጉም፤ ስለዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣህባቸው።
እንዳዘዘኝም አደረግሁ፤ ቀን ለቀንም እክቴን እንደ ስደተኛ እክት አወጣሁ፤ በማታም ጊዜ ግንቡን በእጄ ነደልሁ፤ በጨለማም አወጣሁት፤ በፊታቸውም በትከሻዬ ላይ አንግቼ ተሸከምሁት።
ለእናንተ ለወዳጆች እላችኋለሁ፦ ሥጋችሁን የሚገድሉትን አትፍሩአቸው፤ ከዚህም የበለጠ ማድረግ የሚችሉት የላቸውም።
ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለ የሚጠብቀውም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”
እኔ እንደምሄድ ወደ እናንተም እንደምመለስ የነገርኋችሁን ሰምታችኋል፤ ብትወዱኝስ ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር፤ እርሱ አብ ይበልጠኛልና።