La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዩኤል 1:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከተ​ምች የቀ​ረ​ውን አን​በጣ በላው፤ ከአ​ን​በ​ጣም የቀ​ረ​ውን ደጎ​ብያ በላው፤ ከደ​ጎ​ብ​ያም የቀ​ረ​ውን ኩብ​ኩባ በላው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከአንበጣ መንጋ የተረፈውን፣ ትልልቁ አንበጣ በላው፤ ከትልልቁ አንበጣ የተረፈውን፣ ኵብኵባ በላው፤ ከኵብኵባ የተረፈውን፣ ሌሎች አንበጦች በሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከተምች የቀረውን አንበጣ በላው፥ ከአንበጣም የቀረውን ደጎብያ በላው፥ ከደጎብያም የቀረውን ኩብኩባ በላው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከተምች መንጋ የተረፈውን ሰብል፥ የሚርመሰመስ የአንበጣ መንጋ በላው፤ ከዚያ የተረፈውን እንደ ውሽንፍር የሚገርፍ የአንበጣ መንጋ አጠፋው፤ ከዚያም የተረፈውን ኲብኲባ በላው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከተምች የቀረውን አንበጣ በላው፥ ከአንበጣም የቀረውን ደጎብያ በላው፥ ከደጎብያም የቀረውን ኩብኩባ በላው።

Ver Capítulo



ኢዩኤል 1:4
19 Referencias Cruzadas  

“በም​ድር ላይም ራብ፥ ወይም ቸነ​ፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረ​ማሞ ቢሆን፥ አን​በጣ፥ ወይም ኩብ​ኩባ ቢመጣ፥ የሕ​ዝ​ብ​ህም ጠላት ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው በአ​ን​ዲቱ ከብቦ ቢያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው፥ መቅ​ሠ​ፍ​ትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥


“በም​ድር ላይ ራብ፥ ወይም ቸነ​ፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረ​ማሞ፥ ወይም አን​በጣ፥ ወይም ኩብ​ኩባ ቢሆን፥ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የሀ​ገ​ሩን ከተ​ሞች ከብ​በው ቢያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ቸው፥ ማና​ቸ​ውም መቅ​ሠ​ፍ​ትና ደዌ ቢሆን፥


ዝናብ እን​ዳ​ይ​ወ​ርድ ሰማ​ያ​ቱን ብዘጋ፥ ወይም የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን እን​ጨት ሁሉ ይበላ ዘንድ አን​በ​ጣን ባዝ​ዘው፥ ወይም በሕ​ዝቤ ላይ ቸነ​ፈር ብሰ​ድድ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ላ​ቸው አሕ​ዛ​ብን አላ​ጠ​ፉም፤


ሕዝ​ቤን ለመ​ል​ቀቅ እንቢ ብትል ግን፥ እነሆ፥ ነገ በዚህ ጊዜ በተ​ራ​ራ​ዎ​ችህ ሁሉ ላይ አን​በ​ጣን አመ​ጣ​ለሁ፤


የም​ድ​ሩ​ንም ፊት ይሸ​ፍ​ናል፤ ምድ​ሩን ለማ​የት አይ​ቻ​ልም፤ ከበ​ረ​ዶ​ውም ተርፎ በም​ድር ላይ የቀ​ረ​ላ​ች​ሁን ትርፍ ሁሉ ይበ​ላል፤ ያደ​ገ​ላ​ች​ሁ​ንም የእ​ር​ሻ​ውን ዛፍ ሁሉ ይበ​ላል፤


አን​በጣ እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ሰብ ትን​ሹም ትል​ቁም ምር​ኮ​አ​ችሁ እን​ዲሁ ይሰ​በ​ሰ​ብ​ላ​ች​ኋል።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል በራሱ ምሎ​አል፦ በእ​ው​ነት ሰዎ​ችን እንደ አን​በጣ እሞ​ላ​ብ​ሻ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም እየ​ሮጡ ይወ​ር​ዱ​ብ​ሻል።”


“በም​ድር ላይ ዓላ​ማን አንሡ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል መለ​ከ​ትን ንፉ፤ አሕ​ዛ​ብ​ንም ለዩ​ባት፤ የአ​ራ​ራ​ት​ንና የሚ​ኒን የአ​ስ​ከ​ና​ዝ​ንም መን​ግ​ሥ​ታት እዘ​ዙ​ባት፤ ጦረ​ኞ​ች​ንም በላ​ይዋ አቁሙ፤ ብዛ​ታ​ቸው እንደ አን​በጣ የሆኑ ፈረ​ሶ​ችን በላ​ይዋ አውጡ።


የሰ​ደ​ድ​ሁ​ባ​ችሁ ታላቁ ሠራ​ዊቴ አን​በ​ጣና ደጎ​ብያ፥ ኩብ​ኩ​ባና ተምች ስለ በላ​ቸው ዓመ​ታት እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


በአ​ባ​ርና በቸ​ነ​ፈር መታ​ኋ​ችሁ፤ አት​ክ​ል​ታ​ችሁ፥ ወይ​ና​ች​ሁና በለ​ሳ​ችሁ፥ ወይ​ራ​ች​ሁም ከበጀ በኋላ ተምች በላው፤ ይህም ሆኖ እና​ንተ ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም ከም​ሥ​ራቅ አን​በጣ ይመ​ጣል፤ አን​ዱም ኵብ​ኵባ ንጉሡ ጎግ ነበረ።


ስለ እናንተ ነቀዙን እገሥጻለሁ፥ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፣ በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ብዙ ዘርም ወደ እርሻ ታወ​ጣ​ለህ፤ አን​በ​ጣም ይበ​ላ​ዋ​ልና ጥቂት ትሰ​በ​ስ​ባ​ለህ።


ዛፍ​ህን ሁሉ፤ የም​ድ​ር​ህ​ንም ፍሬ ሁሉ ኩብ​ኩባ ያጠ​ፋ​ዋል።