Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 7:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዝናብ እን​ዳ​ይ​ወ​ርድ ሰማ​ያ​ቱን ብዘጋ፥ ወይም የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን እን​ጨት ሁሉ ይበላ ዘንድ አን​በ​ጣን ባዝ​ዘው፥ ወይም በሕ​ዝቤ ላይ ቸነ​ፈር ብሰ​ድድ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማያትን በምዘጋበት ጊዜ ወይም ምድሪቱን እንዲበላ አንበጣ በማዝዝበት ጊዜ፣ ወይም በሕዝቤ ላይ ቸነፈር በምሰድድበት ጊዜ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ዝናብ እንዳይወርድ ሰማያቱን ብዘጋ፥ ወይም ምድሪቱን እንዲበላ አንበጣን ባዝዘው፥ ወይም በሕዝቤ ላይ ቸነፈር ብሰድድ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማያትን በምዘጋበት ጊዜ፥ ወይም ሰብሉን እንዲበላ አንበጣ በምልክበት ጊዜ፥ ወይም ቸነፈር በሕዝቤ ላይ በማወርድበት ጊዜ ሁሉ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ዝናብ እንዳይወርድ ሰማያቱን ብዘጋ፥ ወይም ምድሪቱን ይበላ ዘንድ አንበጣን ባዝዘው፥ ወይም በሕዝብ ላይ ቸነፈር ብሰድድ፥

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 7:13
17 Referencias Cruzadas  

እርሱ ሁሉን ቢገ​ለ​ብጥ፥ ምን አደ​ረ​ግህ? የሚ​ለው ማን ነው?


እነሆ፥ እርሱ ቢያ​ፈ​ርስ፥ ማን ይሠ​ራል? በሰ​ውም ላይ ቢዘ​ጋ​በት ማን ይከ​ፍ​ታል?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ላ​ቸው አሕ​ዛ​ብን አላ​ጠ​ፉም፤


የሰ​ደ​ድ​ሁ​ባ​ችሁ ታላቁ ሠራ​ዊቴ አን​በ​ጣና ደጎ​ብያ፥ ኩብ​ኩ​ባና ተምች ስለ በላ​ቸው ዓመ​ታት እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


መከር ሳይ​ደ​ርስ ገና ከሦ​ስት ወር በፊት ዝና​ብን ከለ​ከ​ል​ኋ​ችሁ፤ በአ​ን​ድም ከተማ ላይ አዘ​ነ​ብሁ፤ በሌ​ላ​ውም ከተማ ላይ እን​ዳ​ይ​ዘ​ንብ አደ​ረ​ግሁ፤ በአ​ንድ ወገን ዘነበ፤ ያል​ዘ​ነ​በ​በ​ትም ወገን ደረቀ።


በሞት እቀ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም፤ አን​ተ​ንና የአ​ባ​ት​ህን ቤት ግን ለታ​ላ​ቅና ከዚህ ለሚ​በዛ ሕዝብ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ” አለው።


እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በነ​ቢዩ በኤ​ል​ያስ ዘመን በም​ድር ሁሉ ብርቱ ረኃብ እስ​ኪ​ሆን ድረስ ሰማይ ሦስት ዓመት ከስ​ድ​ስት ወር በተ​ዘ​ጋ​በት ጊዜ ብዙ መበ​ለ​ቶች በእ​ስ​ራ​ኤል ውስጥ ነበሩ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ እን​ዳ​ይ​ነ​ድ​ድ​ባ​ችሁ፥ ዝና​ብም እን​ዳ​ይ​ዘ​ንብ፥ ምድ​ሪ​ቱም ፍሬ​ዋን እን​ዳ​ት​ሰጥ ሰማ​ይን እን​ዳ​ይ​ዘ​ጋ​ባ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር ፈጥ​ና​ችሁ እን​ዳ​ት​ጠፉ ተጠ​ን​ቀቁ።


እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ሊዘጉ ሥልጣን አላቸው፤ ውሕሃዎችንም ወደ ደም ሊለውጡ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሠፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ ሥልጣን አላቸው።


“በፊላደልፊያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ የዳዊት መክፈቻ ያለው፥ የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል፦


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos