ኤርምያስ 50:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰይፍ በተዋጊዎችዋ ላይ አለ፤ እነርሱም ይደክማሉ። ሰይፍም በኀያላኖችዋ ላይ አለ፤ እነርሱም ይደነግጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰይፍ በሐሰተኞች ነቢያቷ ላይ መጣ! እነርሱም ሞኞች ይሆናሉ፤ ሰይፍ በጦረኞቿ ላይ ተመዘዘ፤ እነርሱም ይሸበራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰይፍ በምዋርተኞች ላይ አለ ሞኞችም ይሆናሉ፥ ሰይፍም በኃያላኖችዋ ላይ አለ እነርሱም ይጠፋሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሟርተኞቻቸው ሞኞች ይሆኑ ዘንድ ወታደሮቻቸውም በፍርሃት ይርበደበዱ ዘንድ ሰይፍ በእነርሱ ላይ ይመዘዝ!። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰይፍ በሚጓደዱት ላይ አለ ሰነፎችም ይሆናሉ፥ ሰይፍም በኃያላኖችዋ ላይ አለ እነርሱም ይደነግጣሉ። |
አቤሴሎምና የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ “የአርካዊው የኩሲ ምክር ከአኪጢፌል ምክር ይሻላል” አሉ። እግዚአብሔርም በአቤሴሎም ላይ ክፉ ያመጣ ዘንድ እግዚአብሔር መልካሚቱን የአኪጦፌልን ምክር እንዲበትን አዘዘ።
እርሱም ይህን ሲናገር ንጉሡ አሜስያስ፥ “በውኑ የንጉሡ አማካሪ ልትሆን ሹሜሃለሁን? ቅጣት እንዳያገኝህ ተጠንቀቅ” አለው። ነቢዩም፥ “ይህን አድርገሃልና፥ ምክሬንም አልሰማህምና እግዚአብሔር ሊያጠፋህ እንዳሰበ አወቅሁ” ብሎ ዝም አለ።
የእስራኤል ቅዱስ፥ የሚቤዣችሁ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ስለ እናንተ ወደ ባቢሎን ሰድጃለሁ፤ ስደተኞችን አስነሣለሁ፤ ከለዳውያንም በመርከብ ውስጥ ይታሰራሉ።
በሟርት ሙት እናስነሣለን የሚሉትን፥ ከልባቸውም አንቅተው ሐሰት የሚናገሩትን ሰዎች ምልክት የሚለውጥ ማን ነው? ጥበበኞቹንም ወደ ኋላ ይመልሳል፤ ምክራቸውንም ስንፍና ያደርጋል።
እነሆ እንደ ንስር ወጥቶ ይመለከታል፤ ክንፉንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፤ በዚያም ቀን የኤዶምያስ ኀያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።
በአንቺም እረኛውንና መንጋውን እበትናለሁ፤ በአንቺም አራሹንና ጥማዱን እበትናለሁ፤ በአንቺም አለቆችንና መሳፍንትን እበትናለሁ።
የባቢሎን ተዋጊዎች መዋጋትን ትተዋል፤ በአምባዎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኀይላቸውም ጠፍቶአል፤ እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል፤ መወርወሪያዎችዋም ተሰብረዋል።
በትዕቢት ተነፍቶአል፤ አንዳችም አያውቅም፤ ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፤ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ።
አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።
ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”