ኤርምያስ 48:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በርራ እንድትወጣ ለሞአብ ክንፍ ስጡአት፤ ከተሞችዋም ባድማ ይሆናሉ፤ የሚኖርባቸውም የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርራ እንድታመልጥ፣ ለሞዓብ ክንፍ ስጧት፤ ከተሞቿም ምንም እስከማይኖርባቸው ድረስ፣ ባድማ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በርራ እንድትወጣ ለሞዓብ ክንፍ ስጡአት፤ ከተሞችዋም ሰው የማይኖርባቸው ባድማ ይሆናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠፍ እንድትሆን በሞአብ አገር ላይ ጨው ነስንሱባት፤ ከተሞችዋም ሰው የማይኖርባቸው ባድማ ይሆናሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በርራ እንድትወጣ ለሞዓብ ክንፍ ስጡአት፥ ከተሞችዋም ባድማና ወና ይሆናሉ። |
እግዚአብሔርም ከእንግዲህ ወዲህ የሥራችሁን ክፋትና ያደረጋችሁትን ርኵሰት ይታገሥ ዘንድ አልቻለም፤ ስለዚህ ምድራችሁ ባድማ፥ በረሃና መረገሚያ ሆናለች፤ እስከ ዛሬም የሚኖርባት የለም።
አንቺ በግብፅ የምትቀመጪ ልጅ ሆይ! ሜምፎስ ባድማ ትሆናለችና፥ የሚቀመጥባትም አይገኝምና ለፍልሰት የሚሆን ዕቃ አዘጋጂ።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በእርግጥ ሞዓብ እንደ ሰዶም፥ የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ፥ የሳማ ስፍራና የጨው ጕድጓድ ለዘላለምም ምድረ በዳ ሆነው ይኖራሉ፣ የሕዝቤም ቅሬታ ይበዘብዛቸዋል፥ ከወገኔም የተረፉት ይወርሱአቸዋል።
ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሓ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።