La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 39:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ውሰ​ደ​ውና በመ​ል​ካም ተመ​ል​ከ​ተው፤ የሚ​ል​ህ​ንም ነገር አድ​ር​ግ​ለት እንጂ ክፉን ነገር አታ​ድ​ር​ግ​በት።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ውሰደውና እንክብካቤ አድርግለት፤ የሚፈልገውን ነገር ፈጽምለት እንጂ አትጕዳው።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ውሰደው፥ በበጎ ተመልከተው፥ የሚሻውንም ነገር አድርግለት እንጂ ምንም ዓይነት ክፉ ነገር አታድርግበት።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ሂድ፥ ኤርምያስን ፈልገህ አግኘውና ተገቢውን ጥንቃቄ አድርግለት፤ እርሱ የሚፈልገውን ሁሉ አድርግለት እንጂ በምንም ነገር እንዳትጐዳው።”

Ver Capítulo



ኤርምያስ 39:12
12 Referencias Cruzadas  

ቅንነትን የሚሹ ሰላምን ያገኛሉ።


የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሽ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ወደ ወደደውም ይመልሳታል፥ በዚያም ትቈያለች።


በእርሱ ላይ ዐይንህን ብታተኩር አታገኘውም፥ ለእርሱ የንስር ክንፍ ተዘጋጅቶለታልና። ወደሚቆምበትም ቤት ይመለሳልና።


አቤቱ! በመ​ከ​ራ​ቸ​ውና በጭ​ን​ቃ​ቸው ጊዜ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ዘንድ ስለ እነ​ርሱ በጎ ነገር በአ​ንተ ፊት የቆ​ምሁ ባል​ሆን ይህ ለእ​ነ​ርሱ መከ​ና​ወን ይሁን።


ከክፉ ሰዎ​ችም እጅ እታ​ደ​ግ​ሃ​ለሁ፤ ከጨ​ካ​ኞ​ችም ጡጫ እቤ​ዥ​ሃ​ለሁ።


ዐይ​ኔ​ንም ለበ​ጎ​ነት በእ​ነ​ርሱ ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ወደ​ዚ​ህ​ችም ምድር ለመ​ል​ካም እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እሠ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ አላ​ፈ​ር​ሳ​ቸ​ውም፤ እተ​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ አል​ነ​ቅ​ላ​ቸ​ውም።


የአ​ዛ​ዞች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም ላከ፤ ናቡ​ሻ​ዝ​ባ​ንም፥ ራፋ​ስ​ቂ​ስም፥ ኔር​ጋል ሴራ​አ​ጼ​ርም፥ ራብ​ማ​ግም፥ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ አለ​ቆች ሁሉ ላኩ።


አሁ​ንም እነሆ በእ​ጅህ ካለ​ችው ሰን​ሰ​ለት ዛሬ ፈታ​ሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢ​ሎን መም​ጣት መል​ካም መስሎ ቢታ​ይህ፥ ና፤ እኔም በመ​ል​ካም አይ​ሃ​ለሁ፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢ​ሎን መም​ጣት መል​ካም መስሎ ባይ​ታ​ይህ ግን፥ ተቀ​መጥ፤ ተመ​ል​ከት፥ እነሆ፥ ሀገ​ሪቱ ሁሉ በፊ​ትህ ናት፤ ትሄድ ዘንድ መል​ካም መስሎ በሚ​ታ​ይ​ህና ደስ በሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህም ስፍራ ተቀ​መጥ።”


በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ፊት ተማ​ር​ከው ቢሄዱ በዚያ ሰይ​ፍን አዝ​ዛ​ታ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋም ትገ​ድ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ ዐይ​ኔ​ንም ለመ​ል​ካም ሳይ​ሆን ለክ​ፋት በእ​ነ​ርሱ ላይ እጥ​ላ​ለሁ።”


ከመ​ከ​ራ​ውም ሁሉ አዳ​ነው፤ በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ፊትም ሞገ​ስ​ንና ጥበ​ብን ሰጠው፤ በግ​ብ​ፅና በቤቱ ሁሉ ላይ ቢት​ወ​ደድ አድ​ርጎ ሾመው።