ኤርምያስ 36:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስም የኔርዩን ልጅ ባሮክን ጠራ፤ ባሮክም እግዚአብሔር ለእርሱ የተናገረውን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ በመጽሐፉ ክርታስ ጻፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስም የኔርያን ልጅ ባሮክን ጠራው፤ ባሮክም እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ ተቀብሎ በብራናው ላይ ጻፈ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስም የኔርያን ልጅ ባሮክን ጠራ፥ ባሮክም ኤርምያስ እየነገረው ጌታ ለእርሱ የተናገረውን ቃላት ሁሉ በመጽሐፉ ክርታስ ጻፈ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም የኔሪያን ልጅ ባሮክን ጠርቼ እግዚአብሔር የነገረኝን ቃል ሁሉ አንድ በአንድ እየነገርኩት በሚጠቀለል ብራና ጻፈው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስም የኔርያን ልጀ ባሮክን ጠራ፥ ባሮክም እግዚአብሔር ለእርሱ የተናገረውን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ በመጽሐፉ ክርታስ ጻፈ። |
በእርስዋም ላይ የተናገርሁትን ቃሌን ሁሉ፥ ኤርምያስ በአሕዛብ ሁሉ ላይ በትንቢት የተናገረውን በዚች መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ፥ በዚያች ምድር ላይ አመጣለሁ።
የአጎቴም ልጅ አናምኤል፥ የውሉንም ወረቀት የፈረሙ ምስክሮች፥ በግዞት ቤት አደባባይ የተቀመጡ አይሁድም ሁሉ እያዩ የውሉን ወረቀት ለማሴው ልጅ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት።
አለቆቹም ሁሉ፥ “በሕዝቡ ጆሮ ያነበብኸውን ክርታስ በእጅህ ይዘህ ና” ብለው የኩሲ ልጅ የሰሌምያ ልጅ የናታንያ ልጅ ይሁዳን ወደ ኔርዩ ልጅ ወደ ባሮክ ላኩ። የኔርዩም ልጅ ባሮክ ክርታሱን በእጁ ይዞ ወደ እነርሱ ወረደ።
ንጉሡም ክርታሱን ያመጣ ዘንድ ይሁዳን ላከ፤ እርሱም ከጸሓፊው ከኤሊሳማ ክፍል ወሰደው፤ ይሁዳም በንጉሡና በንጉሡ አጠገብ በቆሙት አለቆች ሁሉ ጆሮ አነበበው።
ይሁዳም ሦስትና አራት ዐምድ ያህል በአነበበ ቍጥር፥ ንጉሡ በብርዕ መቍረጫ ቀደደው፤ ክርታሱንም በምድጃ ውስጥ በአለው እሳት ፈጽሞ እስኪቃጠል ድረስ በምድጃ ውስጥ ወደ አለው እሳት ጣለው።
ንጉሡም ጸሓፊውን ባሮክንና ነቢዩን ኤርምያስን ይይዙ ዘንድ የንጉሡን ልጅ ይረሕምኤልንና የዓዝርኤልን ልጅ ሠራያን የዓብድኤልንም ልጅ ሰሌምያን አዘዘ፤ እግዚአብሔር ግን ሰወራቸው።
ንጉሡም፥ ባሮክ ከኤርምያስ አፍ የጻፈው ቃል ያለበትን ክርታስ ካቃጠለ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦
“ዳግመኛም ሌላ ክርታስ ውሰድ፤ የይሁዳም ንጉሥ ኢዮአቄም በአቃጠለው ክርታስ ላይ የነበረውን የቀድሞውን ቃል ሁሉ ጻፍበት።
ኤርምያስም ሌላ ክርታስ ወሰደ፤ ለኔርዩም ልጅ ለጸሓፊው ለባሮክ ሰጠው፤ እርሱም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ያቃጠለውን የመጽሐፉን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ ጻፈበት፤ ደግሞም እንደ ቀድሞው ያለ ቃል ብዙ ቃል ተጨመረበት።
አንተ ግን ገብተህ ከአፌ የጻፍኸውን የእግዚአብሔርን ቃል በጾም ቀን በእግዚአብሔር ቤት በሕዝቡ ጆሮ በክርታሱ አንብብ፤ ደግሞም ከከተሞቻቸው በሚወጡ በይሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አንብበው።
ነገር ግን ከለዳውያን እንዲገድሉን ወደ ባቢሎንም እንዲያፈልሱን በእጃቸው አሳልፈህ ትሰጠን ዘንድ የኔርዩ ልጅ ባሮክ በላያችን ላይ አነሣሥቶሃል” አሉት።
የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ከእርሱ ዘንድ ወደ ባቢሎን በሄደ ጊዜ ለማሴው ልጅ ለኔርዩ ልጅ ለሠራያ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘው ቃል ይህ ነው።
ሠራያም የቤቱ አዛዥ ነበረ፤ በባቢሎንም ላይ የሚመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስለ ባቢሎን የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ ኤርምያስ በአንድ መጽሐፍ ላይ ጻፈው።