ኤርምያስ 31:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ከሰሜን ሀገር አመጣቸዋለሁ፤ ከምድርም ዳርቻ ለበዓለ ፋሲካ እሰበስባቸዋለሁ፤ ብዙ አሕዛብም ይወለዳሉ፤ ወደዚህም ይመለሳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ ከሰሜን ምድር አመጣቸዋለሁ፤ ከምድርም ዳርቻ እሰበስባቸዋለሁ፤ በመካከላቸውም ዕውሮችና ዐንካሶች፣ ነፍሰ ጡርና በምጥ ላይ ያሉ ሴቶች ይገኛሉ፤ ታላቅም ሕዝብ ሆነው ይመለሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ ከሰሜን አገር አመጣቸዋለሁ፤ ከምድርም ዳርቻ እሰበስባቸዋለሁ፤ በመካከላቸውም ዓይነ ስውርና አንካሳው ያረገዘችና ምጥ የያዛትም በአንድነት ይሆናሉ፤ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ ከሰሜን አመጣቸዋለሁ፤ ከምድር ዳርቻም እሰበስባቸዋለሁ፤ ዕውሮች፤ አንካሶች፥ ነፍሰጡሮችና በምጥ የተያዙ ሴቶች ሁሉ ከእነርሱ ጋር አብረው ይመጣሉ፤ ታላቅ ሕዝብ ሆነው ወደ አገራቸው ይመለሳሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ከሰሜን አገር አመጣቸዋለሁ፥ ከምድርም ዳርቻ እሰበስባቸዋለሁ፥ በመካከላቸውም ዕውሩና አንካሳው ያረገዘችና የወለደችም በአንድነት፥ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ። |
ዕውሮችንም በማያውቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ የማያውቋትንም ጎዳና እንዲረግጡ አደርጋቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህንም አደርግላቸዋለሁ፤ አልተዋቸውምም።
እግዚአብሔር የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፤ በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን ማዳን ያያሉ።
ነገር ግን፥ “የእስራኤልን ልጆች ከሰሜን ምድር፥ ከተሰደዱበትም ምድር ሁሉ ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን! ይባላል፤ እኔም ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።
የሕዝቤን ቅሬታ ከበተንኋቸው ምድር ሁሉ ወደ መሰማሪያቸው ሰብስቤ እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም ይበዛሉ፤ ይባዛሉም።
ነገር ግን፥ “የእስራኤልን ቤት ዘር ከሰሜን ሀገርና ካሳደዷቸውም ሀገር ሁሉ ያወጣና የመራ ሕያው እግዚአብሔርን!” ይባላል፤ በምድራቸውም መልሶ ያኖራቸዋል።
እገለጥላችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ምርኮአችሁንም እመልሳለሁ፤ ከአሕዛብ ሁሉ ዘንድ እናንተንም ከበተንሁበት ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ እናንተንም ለምርኮ ወዳፈለስሁበት ስፍራ እመልሳችኋለሁ።
ሂድና ይህን ቃል ወደ ሰሜን ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ከዳተኛዪቱ እስራኤል ሆይ! ወደ እኔ ተመለሽ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ መሓሪ ነኝና፥ ለዘለዓለምም አልቈጣምና በእናንተ ላይ ፊቴን አላጸናም፥” ይላል እግዚአብሔር።
በዚያም ዘመን የይሁዳ ቤት ወደ እስራኤል ቤት ይሄዳል፤ በአንድም ሆነው ከሰሜን ምድር ርስት አድርጌ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።
ከአሕዛብም ዘንድ አወጣችኋለሁ፤ ከተበተናችሁባትም ሀገር ሁሉ በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ፥ በፈሰሰችም መዓት እሰበስባችኋለሁ።
ከአሕዛብ ዘንድ ባወጣኋችሁ ጊዜ፥ ከተበተናችሁባትም ሀገር ሁሉ በሰበሰብኋችሁ ጊዜ እንደ ጣፋጭ ሽታ እቀበላችኋለሁ፤ በአሕዛብም ፊት እቀደስባችኋለሁ።
በደመናና በጭጋግ ቀን እረኛ ከበጎቹ መካከል የተለየውን እንደሚፈልግ፥ እንደዚሁ በጎችን እፈልጋለሁ፤ በደመናና በጭጋግ ቀን ከተበተኑባቸው ሀገሮች ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ።
ከአሕዛብም ዘንድ አወጣቸዋለሁ፤ ከሀገሮችም ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ገዛ ሀገራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤልም ተራሮች ላይ፥ በፈሳሾችም አጠገብ፥ በምድርም ላይ ሰዎች በሚኖሩባት ስፍራ ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።
የጠፋውንም እፈልጋለሁ፤ የባዘነውንም እመልሳለሁ፤ የተሰበረውንም እጠግናለሁ፤ የደከመውንም አጸናለሁ፤ የወፈረውንና የበረታውንም እጠብቃለሁ፤ በፍርድም እጠብቃቸዋለሁ።”
በዚያ ዘመን እነሆ፥ ባስጨነቁሽ ሁሉ ላይ አደርግባቸዋለሁ፣ አንካሳይቱንም አድናለሁ፥ የተጣለችውንም እሰበስባታለሁ፣ ባፈሩባትም ምድር ሁሉ ላይ ለምስጋናና ለከበረ ስም አደርጋቸዋለሁ።
ምሳም ከበሉ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ፦ ስምዖን ጴጥሮስን፥ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?” አለው፤ እርሱም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “በጎችን ጠብቅ” አለው።
አንተ አማኙ በጣዖት ቤት በማዕድ ተቀምጠህ ያየህ ቢኖር ያ ልቡ ደካማ የሆነ ሰው ወዲያው ለጣዖት የተሠዋውን ደፍሮ ይበላል።
ወንድሞች ሆይ! እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዐት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።
ሊቀ ካህናታችን ለድካማችን መከራ መቀበልን የማይችል አይደለምና፤ ነገር ግን ከብቻዋ ከኀጢአት በቀር እኛን በመሰለበት ሁሉ የተፈተነ ነው።